አሜሪካዊቷ ቫኒሳ ዊልያምስ ለህዳሴው ግድብ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው እንደሚሠሩ ቃል ገቡ

አሜሪካዊቷ ቫኒሳ ዊልያምስ ለህዳሴው ግድብ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው እንደሚሠሩ ቃል ገቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ለኢትዮጵያ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሆነው እንደሚሠሩ በአሜሪካ የጥቁር ከንቲባዎች ኮንፈረንስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተናገሩ።

በጥቁር ከንቲባዎች ብሔራዊ ኮንፈረንስ ዳይሬክተሮች ቦርድ እና አጋር አገራት እ.ኤ.አ. በሰኔ 19፣ 2011 የተመሰረተው የጥቁር ከንቲባዎች ኮንፈረንስ ዋና ሥራ አስፈፃሚና እና ጸሐፊ የሆኑት ቫኒሳ ዊሊያምስ፤ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አስመሌክቶ በተካሄደው ውይይት፣ በውሃ አጠቃቀሙ ዙሪያ በሚነሱ ጉዳዮች ለኢትዮጵያ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሆነው ለመሥራት ቃል መግባታቸው ተሰምቷል።
አፍሪካውያን ጥራት ያለው ህይወት እንዳይኖሩ እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮችን ሲመለከት ኮንግረሳቸው ሐሳቡን እንደሚገልፅ የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፤ አፍሪካውያን ያልተገቡ ነገሮችን ስናይ በጋራ ልንቆም ይገባል ሲሉም በአቋም ረገድ የህዳሴው ግድብ ጥቅም የጋራ መሆኑን አመላክተዋል።
  “ለእናንተ ጥቅም አብረን እንቆማለን፤ ለእናንተ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር በመሆን ውሃችሁን እንድትጠቀሙ ለሌላው ዓለም ድምፅ ለመሆን እንሠራለን” ያሉት ቫኒሳ ዊሊያምስ፤ የበጎ ፍቃድ አምባሳደርነታቸውንም በደስታ እንደሚወጡት አረጋግጠዋል።
በአሁኑ ጊዜ የሚድልፊልድ አላባማ ከንቲባ በሆኑት ጋሪ ሪቫርድሰን ፕሬዚዳንትነት የሚመራው የጥቁር ከንቲባዎች ኮንፈረንስ ሲመሰረት ትምህርትና ኢኮኖሚን ለማጎልበት፣ ሥልጠና እና ቱሪዝም ላይ ለመሥራት የሚያስችል መደላድል ለመፍጠር፣ በርቀትና ቋንቋ ልዩነት እና የሀብት እጥረት ምክንያት የሚፈጠር ልዩነትን ለማስወገድ፣ የተሻለ የኑሮ ጥራት እና ዘላቂ ልማት ለማምጣት አስፈላጊ የሆኑትን ሀብቶች፣ ችሎታዎች እና ክህሎቶች ለማገናኘት እንደ መተላለፊያ መስመር ሆኖ ለማገልገል መሆኑ ይነገራል።

LEAVE A REPLY