ጤና ሚኒስቴር በቀን 15 ሺኅ ሰዎችን ለመመርመር ዝግጅቴን ጨርሻለሁ አለ

ጤና ሚኒስቴር በቀን 15 ሺኅ ሰዎችን ለመመርመር ዝግጅቴን ጨርሻለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የጤና ሚኒስቴር በአገር ዐቀፍ ደረጃ የኮቪድ 19 እለታዊ ምርመራን ወደ 15 ሺኅ ከፍ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን ገለጸ።

ከመጋቢት 4/ 2012 ዓ.ም ጀምሮ የኮሮና ቫይረስ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎችን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በተሰጠው መግለጫ፤  በየጊዜው ቁጥሩ እየጨመረ የመጣውን የመመርመር አቅም በአሁኑ ሰዐት በብሔራዊ ደረጃ 8 ሺኅማድረስ የተቻለ መሆኑ ተነግሯል።
 ከወረርሽኙ መዛመት ጋር ጎን ለጎን የምርመራ አቅምንም ለማሳደግ ተገቢ መሆኑ በመታመኑ፤ በቅርቡ 19 ተጨማሪ ምርመራ ጣቢያዎች ወደ ሥራ እንደሚገቡ እና የምርመራ አቅምንም በቀን ወደ 15 ሺኅ ከፍ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር በመግለጫው ጠቁሟል።
 መንግሥት የችግሩን ጥልቀት አስቀድሞ በመገንዘብ የተለያዩ አደረጃጀቶችን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን ጭምር በማደራጀት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ በሙሉ አቅሙ እየሠራሁ ነው ያለው ሚኒስቴሩ፤ በዚህም መሰረት ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጠጠር ከመደበኛ ባለሙያዎች ውጪ ሌሎች ባለሙያዎችንም አሰልጥኖ ማሰማራት አስፈላጊ በመሆኑ፣ 4 ሺኅ 500 ያክል  ቅጥር ባለሙያዎችን እና 12 ሺኅ የበጎ ፍቃድ ባለሙያዎችን  በማሰልጠን ወደ ሥራ ማሠማራት ችያለሁ ሲል ገልጿል።
በአገር ዐቀፍ ደረጃ በአሁኑ ወቅት  223, ሺኅ 341 የላብራቶሪ ናሙና ምርመራዎች የተካሄዱ ሲሆን፤ ለ767 ሺኅ 708 መንገደኞች የኮቪድ 19 የልየታ ስ ሥራ መሠራቱን፣ ከጥር 15/2012 ዓ.ም ጀምሮ 32 ሚሊዮን ሰዎች በቤት ለቤት ዳሰሳ  መታየታቸውንና ክትትል ለሚስፈልጋቸውም አስፈላጊው ክትትል መደረጉን ተቋሙ በመግለጫው እወቁልኝ ብሏል።
 32,  ሺኅ 957 ሰዎች ቫይረሱ ካለባቸው ሰዎች ንኪኪ ያላቸው በሚል የተለዩ ሲሆን፤   በዚህም አጠቃላይ 4,848 ያክል ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸው 1 ሺኅ 412 ሰዎች ማገገማቸውንና 75 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን ማለፉ ታውቋል።
በተጨማሪም ኮሮና ቫይረስን በአገር ዐቀፍ ደረጃ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በፌደራል፣ በየክልሎችና በየተቋማቱ ያሉትን አደረጃጀቶችና ተቋማት አቅም ለማጠናከርና ለመደገፍ ትኩረት ሰጥቼ እየሠራሁ ነው የሚለው የጤና ሚኒስቴር መግለጫ፤ በተጨማሪም ለኮቪድ -19 ወረርሽኝ ለመከላከል ለሕክምና ግብዓት ግዥ ፤ ለላብራቶሪ ምርመራ እና ለሌሎች ተግባራሮቶች ከፌዴራል መንግሥት ለክልሎች የተለያዩ ድጋፎች መደረጋቸውን አስታውቋል።

LEAVE A REPLY