በህወሓት የተመሰረተው የፌደራሊስቶች ጥምረት ህወሓትን ከጥምረቱ አባረረ

በህወሓት የተመሰረተው የፌደራሊስቶች ጥምረት ህወሓትን ከጥምረቱ አባረረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን ጉባዔ ዛሬ ሲያጠናቅቅ ህወሓት እና ኢዲዩን ከጥምረቱ አባልነት ማገዱን ገለጸ።

በጉባዔው ማጠቃለያ ላይ ጥምረቱ ባወጣው የአቋም መግለጫ፤ ጥምረቱ ሁሉንም ብሔር ብሔረሰቦች አካትቶ በማቀፍ የተሻለ ህብረ ብሔራዊ ፌዴራሊዝም ለመገንባት እና ለብሔር ብሔረሰቦች ተጠቃሚነት ሲል በሰላማዊ መንገድ ለመታገል እየሠራ ቢሆንም፣ ህወሓትና ኢዲዩ የጥምረቱን ጉዞ ለማደናቀፍ ብሎም ጥምረቱን ተጠቅመው አገር ለማተራመስ እየሠሩ ናቸው ሲል ከስሷቸዋል።
እንዲህ ዓይነቱ እንቅስቃሴ በጥምረቱ ዓላማ፣ አሠራርና ደንብ መሰረት ተቀባይነት ያለው ባለመሆኑ ሁለቱ ድርጅቶች ከጥምረቱ እንዲታገዱ ሆኗል ያለው የኢትዮጵያ ፌደራሊስቶች ጥምረት፤ ይህ የጥምረቱ ውሳኔ፣ ማንኛውም ኃይል ጥምረቱን ለግሉ አጀንዳ ማስፈጸሚያ ሊያደርገው እንደማይገባ ማሳያ ብቻ ሳይሆን፤ በአገር ሰላምና ሉዓላዊነት፣ በህዝብ ሰላምና አንድነት ላይ የሚያሴሩ ኃይሎችን አቅፎ የማይሄድ መሆኑን በገሀድ ያረጋግጥኩበት ነው ብሏል።

LEAVE A REPLY