ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– አዲስ አበባ ከተማ እየተባባሰ በመጣው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ ምሰሶ ስርቆት ሳቢያ በበርካታ ቦታዎች የመብራት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ መቋረጡ ተሰማ።
132 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ ምሰሶ በዘራፊዎች ተፈትቶና ተቆርጦ በመውደቁና በተጨማሪም በሌላ ምሰሶ ላይም ጉዳት በማድረሱ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡም ታውቋል።
ይህን ተከትሎ የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ መንደር፣ ሰሚት ኮንዶሚኒየም፣ ቦሌ አራብሳ፣ አየር መንገድ ማህበር፣ ጎሮ፣ አይሲቲ ፓርክ፣ ገርጂ ወረገኑና ገርጂ ካሳንቺስ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል እንደተቋረጠባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ችግሩን ለመፍታት እየሠራ ቢሆንም የተሰረቁትን የምሰሶ ክፍሎች ለመተካት እና ሌሎች የጥገና ሥራዎችን ለመከወን ረጅም ቀናትን የሚወስድበት እንደሆነ ግን ገልጿል።
ተተኪ ምሰሶ በመትከል መስመሩን ለማገናኘት ጥረት እያደረግሁ ነው የሚለው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፤ በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች የኤሌክትሪክ ኃይሉ ተመልሶ እስኪገናኝ ድረስ ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ ምክር ለግሷል።