ከ19 96 ዓ.ም ጀምሮ በኤግዚቢትነት የተያዙ ዕጾችን ጨምሮ ሐሰተኛ ብርና ዶላሮች ተቃጠሉ

ከ19 96 ዓ.ም ጀምሮ በኤግዚቢትነት የተያዙ ዕጾችን ጨምሮ ሐሰተኛ ብርና ዶላሮች ተቃጠሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ በተለያዩ ጊዜያት በኤግዚቢትነት የያዛቸውን አደገኛ ዕፆች እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ማቃጠሉን አስታወቀ።

በወንጀል ምርመራ ቢሮ የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክቶሬት የተደራጁ እና ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ወንጀሎች ምርመራ ዲቪዥን ሓላፊ ኮማንደር በለጠ ጌታቸው፤ ከ2009 ዓ.ም እስከ 2011 ዓ.ም ድረስ ከ139 ተከሳሾች በጥቅል እና በዱቄት መልክ የተያዙ 226 ኪሎ ግራም ኮኬይን፣ 20 በአልባሳት መልክ፣ 10 በመጽሐፍ መልክ የተዘጋጀ ኮኬይን፣ 1249.95 ሚሊ ሊትር በፈሳሽ መልክ የተሠራ ኮኬይን፣ 999.97 ግራም አንፌታሚን፣ 979 ነጥብ 97 ኪሎ ግራም ካናቢስ የተሰኘ አደገኛ ዕፅ እንዲወገድ ተደርጓል ሲሉ አረጋግጠዋል።/
 ከ1996 ዓ.ም እስከ 2002 ዓ.ም ድረስ የተያዙ 23 ሺኅ 505 የኢትዮጵያ ሐሰተኛ የብር ኖት፣ 8 ሺኅ 800 ሐሰተኛ የአሜሪካ ዶላር፣ 9 ሺኅ 970 የኤርትራ ናቅፋ፣ 15 ሺኅ 400 ሐሰተኛ የትራቭል ቼክ፣ 500 የሳዑዲ ሪያል መቃጠሉንም ኮማንደሩ ገልጸዋል።
 ከ1985 እስከ 1994 ዓ.ም ድረስ የተያዙ ሐሰተኛ ማኅተሞች፣ ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶች እና የሕክምና ቁሳቁሶች፣ ጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት፣ የተለያዩ ፓስፖርቶች፣ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው ደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ እንዲወገድ ተደርገዋል።
የምርመራ ቢሮው በዐቃቤ ሕግ እና በፍርድ ቤት በማስወሰን በ1987 ዓ.ም የተያዙ መዝገብ የሌላቸው፣ በኤግዚቢት ላይ ስም ብቻ የተጻፈባቸው መድኃኒቶች እና የሕክምና ቁሳቁሶች፣ የምግብ ዘይት፣ ሌሎች በሕገ ወጥ መንገድ ተይዘው የተገኙ ወታደራዊ አልባሳት፣ ሐሰተኛ ሰነዶች፣ የቴፕ እና የቪዲዮ ካሴቶችም እንዲቃጠሉ ማድረጉን ዛሬ ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY