ዛሬ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ፣ 141 አዲስ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል

ዛሬ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ፣ 141 አዲስ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በኢትዮጵያ ተጨማሪ 141 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውና ሦስት ሰዎች ሕልፈት ሪፖርት መደረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በአዲስ አበባ ነዋሪ፣  የ52 ዓመት ወንድ፣ጰ( በህክምና ላይ የነበረ )፣ የአዲስ አበባ ነዋሪ፣ የ72 ዓመት ወንድ (በህክምና ላይ የነበረ)፣ የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነች የ 62 ዓመት  ሴት (በህክምና ላይ የነበረች) መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሟቾቹን ዝርዝር ይፋ ያደረገበት መግለጫ ያሳያል።
ባለፉት 24 ሰዐታት ዉስጥ ለ 4 ሺኅ 675 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ 139 ኢትዮጲያዉያንና ሁለት የውጭ ሀገራት ዜጎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ከዛሬ ተመዝጋቢዎቹ መሀል 81 ዱ ወንዶች ሲሆኑ 60 ደግሞ ሴቶች ናቸው። እድሜያቸዉም ከ2 ወር እስከ 87 ዓመት የሚደርስ መሆኑ ተረጋግጧል። የመኖሪያ ስፍራቸዉ 113 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 15 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 6 ሰዎች ከሐረሪ ክልል፣ 1 ሰው ከቤንሻንጉል፣ 1 ሰው ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር፣ 3 ሰዎች ከጋምቤላ ክልል፣ 2 ሰዎች ከሶማሊ ክልል መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

LEAVE A REPLY