የሶደሬ ሪዞርትና የሪፍት ቫሊ ዮንቨርስቲ ባለቤት ገመናን በዋልታ ቲቪ እንዳይተላለፍ ያገደው የፍርድ...

የሶደሬ ሪዞርትና የሪፍት ቫሊ ዮንቨርስቲ ባለቤት ገመናን በዋልታ ቲቪ እንዳይተላለፍ ያገደው የፍርድ ቤት እግድ ተሻረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በሶደሬ ሪዞርትና የሪፍት ቫሊ ዮንቨርስቲ ኮሌጅ ባለቤት በሆኑት በአቶ ድንቁ ዙሪያ የተሠራውና በዋልታ ቴሌቪዥን እንዳይተላለፍ የታገደው ተከታታይ ፕሮግራም እግዱ ተነሳለት።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ የፍታብሔር ችሎት ዛሬ ባስተላለፈው ውሳኔ፤ ዋልታ ቴሌቪዥን ያዘጋጀው የምርመራ ዘገባ እንዳይተላለፍ አሳልፎት የነበረውን እግድ የፕሬስ ህጉን የሚጣረስ ሆኖ ስላገኘሁት አንስቼዋለሁ ብሏል።
ለእይታ የሚበቃው ፕሮግራም ገና ለገና የግለሰብን ስምና ምግባር ያጎድፋል በሚል ከወዲሁ ግምት መውሰድ የማይቻል ከመሆኑም ባሻገር፣ በፕሬስ ሕጉ የሰፈረውን የመናገር፣ የመጻፍ እና ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን የሚጻረር በመሆኑ ችሎቱን እንዳነሳ አስታውቋል።
የሚዲያ ህጉ በተሰጠው ግዴታና ሓላፊነት የምርመራ ዘገባው ቀጣይ (3ኛ) ክፍል ሊተላለፍ እንደሚችል ፍርድ ቤቱ ወስኗል።  ከዚህ ቀደም ዋልታ የፍርድ ቤት እግድ ደርሶት ፕሮግራሙን አስተላለልፏል የሚል ተጨማሪ ክስ ቀርቦበት የነበረ ቢሆንም፤ ከሳሹ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ በተጨማሪነት ክሱን ውድቅ አድርጓል።

LEAVE A REPLY