ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦች በ25 እና በ በ11 ዓመት ከ9 ወር ፅኑ እስራት መቀጣታቸው ተነገረ።
የ64 ዓመቱ ተከሳሽ የሆኑት ግለሰብ ነሐሴ ወር 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዕድሜያቸው ስምንት እና ዘጠኝ አመት የሆኑ ሁለት ሴት ህፃናቶችን በተለያዩ ቀናቶች ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ውስጥ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንደፈጸመባቸው ተረጋግጧል።
ተከሳሹ ላይ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቃቂ ቃሊቲ ምድብ ጽሕፈት ቤት የኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 627(1) ተላልፎ በመገኘቱ አራት ክሶችን መስርቶበታል፡፡
ተከሳሹ ፍርድ ቤት ቀርቦ ክሱን ክዶ ቢከራከርም፣ ዐቃቤ ህግ በተከሳሽ ላይ ማስረጃ አቅርቦ በማሰማቱ እንዲሁም ተከሳሽ የተከሰሰበትን ክስ ሊያስተባብል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን በአራቱም ክሶች ጥፋተኛ ነህ ብሎታል።
በዚህ መሠረት ችሎቱ ተከሳሽ በ60 ዓመት እንዲቀጣ የፈረደበት ቢሆንም፣ የተከሰሰበት ድንጋጌ ጣሪያው 25 ዓመት በመሆኑ በ 25 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ መሰጠቱን አረጋግጠናል።
በተያያዘ ዜና በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 የ15 ዓመት የእንጀራ ልጁን የደፈረው ግለሰብም በ11 ዓመት ከ9 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ሰምተናል።