በኮሮና ምክንያት በተቋረጠው የተማሪዎች ምገባ ሕጻናት ለምግብ አጥረት ተዳርገዋል

በኮሮና ምክንያት በተቋረጠው የተማሪዎች ምገባ ሕጻናት ለምግብ አጥረት ተዳርገዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአዲስ አበባ መስተዳድር ተግባራዊ አድርጎት የነበረዉና በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ከትምህርቱ ጋር አብሮ የተቋረጠው የተማሪዎች ምገባ፤ ደፍኗቸው የነበሩ የችግር ሽንቁሮች ዳግም መከፈታቸው፣ በርካታ ተማሪዎችና ቤተሰቦች ለከፋ ችግር  መጋለጣቸውን አንድ ጥናት አረጋገጠ።

በከተማው ከመዋዕለ ሕፃናት እስከ 8ኛ ክፍል 360 ሺኅ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደረገ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ተጀምሮ እንደነበር ይነገራል።
ይሁንና ባለፈው መጋቢት ኮሮና ቫይረስ መጥቶ ትምህርት ሲቋረጥ ፤ በትምህርት ቤት ምገባው ተጠቃሚ ከነበሩት ተማሪዎች አንዳንዶቹ አሁን ላይ ጎዳና ወጥቶ ምግብ እስከመለመን ለደረሰ ችግር መዳረጋቸውን አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስጠናሁት ያለው ጥናት ያሳያል።
ይኸው ጥናት የትምህርት ቤት ምገባው የሥራ ዕድል ፈጥሮላቸው የነበሩ 12,000 እናቶችም ሥራ አጥ ሆነው ተቸግረዋል ሲል የችግሩን ጥልቀት አመላክቷል።

LEAVE A REPLY