በጀነራል ሰዓረ መኮንን የግድያ ወንጀል ሲካሄድ የነበረው የክርክር ሂደት እንዲቀጥል ተወሰነ

በጀነራል ሰዓረ መኮንን የግድያ ወንጀል ሲካሄድ የነበረው የክርክር ሂደት እንዲቀጥል ተወሰነ

በጀነራል ሰዓረ መኮንን እና በሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ የግድያ ወንጀል ሲካሄድ የነበረው የክርክር ሂደት እንዲቀጥል ተወሰነ

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 248873 1ኛ የፀረ ሽብርና በህገ-መንግስት ላይ የሚፈፀሙ የወንጀል ችሎት በጀነራል ሰዓረ መኮንን እና በሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ የግድያ ወንጀል ሲካሄድ የነበረው የክርክር ሂደት እንዲቀጥል ወሰነ፡፡ ሌሎች ጉዳዮችም እንደነገሩ ሁኔታ በፕላዝማ የክርክር ሂደቱን ለመቀጠል በአመራሩ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

ሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ፍርድ ቤቶች በከፊል በመዘጋታቸው ክርክሩ ለጊዜው ተቋርጦ የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የፌ/ጠ/ዐ/ህግ ክርክሩ እንዲቀጥል ያቀረበውን አቤቱታ በመቀበል የምስክር መስማቱን ሂደት ተከሳሽ በማረሚያ ቤት ሆኖ በፕላዝማ እየታገዘ እንዲቀጥል ችሎቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

የችሎት ክርክሩ ሂደት ከሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ ባሉት ቀናት የተጎጂ ቤተሰቦች እና ጉዳዩን መከታተል የሚፈልጉ ውስን ሚዲያዎች ወይም ግለሰቦች ባሉበት እንደሚቀጥል ከችሎቱ ውሎ ለመረዳት ተችሏል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት

LEAVE A REPLY