የህዳሴው ግድብ ውኃ የሚተኛበት ሥፍራ ደን ምንጣሮ ሥራ ተጀመረ

የህዳሴው ግድብ ውኃ የሚተኛበት ሥፍራ ደን ምንጣሮ ሥራ ተጀመረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውኃ የሚተኛበት ስፍራ ደን ምንጣሮ ሥራ ትናንት መጀመሩ ተነገረ።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሥራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ በሽር አብዱራሂም፤ ክልሉ በኢንተርፕራይዞች አማካኝነት የሚመነጠር 1 ሺኅ ሄክታር መሬት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ተረክቦ ትናንት የምንጣሮ ሥራው እንዲጀመር ተደርጓል ብለዋል።
ግድቡ በመጪው ሐምሌ ውኃ ለመሙላት የተያዘውን እቅድ እንዲሳካ ከወዲሁ የደን ምንጣሮ ሥራውን ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ 2ሺኅ አባላት የያዙ ኢንተርፕራይዞች ወደ ሥራ መግባታቸው ታውቋል።
ኤጀንሲው የምንጣሮ ሥራውን በፍጥነትና በጥራት እንዲከናወን የቅርብ ክትትል ያደርጋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ  የጤና፣ የጸጥታ እና ሌሎችም ቡድኖች ምንጣሮውን ከሚያካሂዱ ኢንተርፕራይዞች ጋር አብረው ወደ ስፍራው መግባታቸውን አስረድተዋል።
ለሥራው የሚያስፈልግ በጀት እና ሌሎች ግብአቶች ለኢንተርፕራይዞቹ መቅረቡን እና አጠቃላይ ለምንጣሮ ሥራው 32 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት እንደተያዘለትም ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
በደን ምንጣሮ ስራው መሳተፍ የጀመሩ ኢንተርፕራይዞች በበኩላቸው ስራውን በአጭር ጊዜ ውስጥ  አጠናቅቀው ለማስረከብ ዝግጁ እንደሆኑ መግለፃቸውን ከኢዜአ ያገኘነው ማስረጃ ያመለክታል።

LEAVE A REPLY