የጄነራል ሰዓረ መኮንንና ሜ/ጀ ገዛኢ አበራ የግድያ ወንጀል ክርክር በፕላዝማ  እንዲካሄድ ተወሰነ

የጄነራል ሰዓረ መኮንንና ሜ/ጀ ገዛኢ አበራ የግድያ ወንጀል ክርክር በፕላዝማ  እንዲካሄድ ተወሰነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ባለፈው ዓመት ሰኔ 15 ቀን አዲስ አበባ ውስጥ የተገደሉት የጦር ኢታማዦር ሹሙ በጀነራል ሰዓረ መኮንን እና በሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ የግድያ ወንጀል ላይ ሲካሄድ የነበረው የክርክር ሂደት እንዲቀጥል መወሰኑ ተነገረ።

ሌሎች ጉዳዮችም እንደ ነገሩ ሁኔታ በፕላዝማ የክርክር ሂደቱ እንዲቀጥል መወሰኑን የጉዳዮ ሓላፊ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ገልጿል።
ሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ፍርድ ቤቶች በከፊል በመዘጋታቸው ክርክሩ ለጊዜው ተቋርጦ እንደነበረ አይዘነጋም።
ይህን ተከትሎ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ክርክሩ እንዲቀጥል ያቀረበውን አቤቱታ በመቀበል የምስክር መስማቱን ሂደት ተከሳሽ በማረሚያ ቤት ሆኖ በፕላዝማ እየታገዘ እንዲቀጥል ችሎቱ ትዕዛዝ መስጠቱ ተሰምቷል።
ከፍርድ ቤት በተገኘ መረጃ መሠረት የችሎት ክርክሩ ሂደት ከሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ ባሉት ቀናት የተጎጂ ቤተሰቦች እና ጉዳዩን መከታተል የሚፈልጉ ውስን ሚዲያዎች ወይም ግለሰቦች ባሉበት እንዲቀጥል ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

LEAVE A REPLY