ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ታሪካዊ ሐውልቶች ላይ ጥቃት የሚደርሱ ተቃዋሚዎችን ማሠር የሚያችል አንቀፅ ያለው ትዕዛዝ ላይ ፊርማቸውን እንዳኖሩ ተሰማ።
አደባባይ የቆመ ማንኛውም ሐውልት ላይ ጉዳት የሚያደርስ ሰው በሕግ ይጠየቃል፤ ለእሥርም ይዳረጋል የሚለው የፕሬዝዳንቱ አዲስ ትዕዛዝ፤ የደቦ ጥቃት የሚያደርሱ ሰዎችን ይዘው ማሰር ያልቻሉ የሕግ አስፈፃሚ አካላት ከፌዴራል መንግሥት ፈንድ እንደሚነፈጋቸውም ገልጿል።
ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ ከተገደለ በኋላ አሜሪካው ውስጥ የተቀጣጠለውን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ሐውልቶች ከጥቅም ውጪ ሆነዋል።
“ይህንን ድርጊት የፈፀሙ በርካታ አመፀኞች፣ ታጣቂዎች እንዲሁም ግራ ዘመም አክራሪዎች ድርጊታቸውን ከተለያዩ ርዕዮተ ዓለሞች ጋር እያቆራኙ ነው። ከእነዚህ አንዱ ደግሞ ለዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ጥፋት የሚመኘው ማርክሲዝም ነው።» የሚለው የትራምፕ በቲውተር የተላለፈ የትዕዛዝ ደብዳቤ ተቃዋሚዎቹን ለታሪካችን ቦታ የማይሰጡ ሲልም ወርፏቸዋል።