ትራንስፎርመር ከአዲስ አበባ በክሬን ጭነው ሊያመልጡ የነበሩ ግለሰቦች ተያዙ

ትራንስፎርመር ከአዲስ አበባ በክሬን ጭነው ሊያመልጡ የነበሩ ግለሰቦች ተያዙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአዲስ አበባ የመብራት ኃይል ሠራተኞች ነን በሚል  ትራንስፎርመር በክሬን ጭነው ለማምለጥ የሞከሩ ግለሰቦች ተያዙ።

በተለያዩ ሥፍራዎች የመብራት ኃይል ሠራተኞች ነን በሚል ማጭበርበሪያ ከመሥሪያ ቤቱ እውቅና ውጭ ኅብረተሰቡ በሚጠቀምበት የኤሌክትሪክ ኃይል ላይ የተለያዩ ወንጀሎችን የሚፈጽሙ ግለሰቦች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ መምጣታቸው ይታወቃል።
በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ሐያት ቁ.1 በሚባል አካባቢ፣ ሰኔ 19/2012 ዓ.ም ከቀኑ 9፤30 አካባቢ ለ80 አባወራዎች አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘውን ትራንስፎርመር ከመሥሪያ ቤቱ እውቅና ውጭ ኮድ3 ኢ.ት84535 በሆነ ክሬን ተሸከርካሪ ታግዘው በመስረቅ ለማምለጥ የሞከሩ ግለሰቦች ለፖሊስ በተሰጠ ጥቆማ  እጅ ከፍንጅ ሊያዙ መቻላቸውን የክፍለ/ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከልና የማኅበረሰብ ዐቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ም/ዳይሬክቶሬት የሆኑት ኮማንደር ያሲን ሁሴን ይፋ አድርገዋል።

LEAVE A REPLY