ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በርካታ አዳዲስ የንግድ እንቅስቃሴዎችን በመጀመር የሚታወቁት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በዓይነቱ የመጀመሪያ ነው የተባለለትን የኢንቨስትመንት ባንክ ለማቋቋም በሂደት ላይ መሆናቸው ታወቀ።
በተለይም በለውጡ ማግስት ከሜቴክ የኢምፔሪያል ሆቴል ግዢ ጋር በተያያዘ ከሌሎች መሰል ባለሀብቶች በተለየ ይቅርታና ምህረትን ተነፍገው በግፍ ረዘም ላለ ጊዜ የታሰሩት ኤርሚያስ አመልጋ ከሕዝብ እና ከዓለም ዐቀፍ ታዋቂ የቢዝነስ ሰዎች (ጃክማን ጨምሮ) በመጋቢት ወር አጋማሽ ከእስር መፈታታቸው ይታወቃል።
የሐሳብ ባለጸጋው ኤርሚያስ አመልጋ፤ በዓይነቱ ልዮ የሆነውን ባንክ ለመመስረት የተሠሩ ሥራዎች መኖራቸውን ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ዛሬ አረጋግጠዋል።
በቅርቡ አዲስ የንግድ እንቅስቃሴን ይዞ ብቅ ስለሚለው ባንካቸው የገለጹት አቶ ኤርሚያስ፤ በኢንቨስትመንት ባንኩ ሥራ እርሳቸውጨእምብዛም ባይገፉበትም፣ በቅርቡ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆን ግን አስታውቀዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በቅርቡ “ኤርሚያስ አመልጋ” የተሰኘ አዲስ ትልቅ ድኅረ ገጽ እንደሚጀምሩና በበርካታ የንግድ ዘርፎች ላይ ለመሥራት በሂደት ላይ መህናቸውን ከእስር ተፈቺው ባለሀብት ተናግረዋል።