የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሶማሌ 35 የአልሻባብ ታጣቂዎችን መግደሉን አስታወቀ

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሶማሌ 35 የአልሻባብ ታጣቂዎችን መግደሉን አስታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከኢትዮጵያ  ወደ ሶማሊያ ሴክተር “ሦስት ባይደዋ”  የተንቀሳቀሰን የኮንቮይ ጉዞ ለማደናቀፍ የሞከሩ  የአልሻባብ ቡድን አባላት ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እርምጃ መወሰዱ ተሰማ።

በሽብር ቡድኑ ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በወሰደው እርምጃ  35 ታጣቂዎች መገደላቸውንና 14 መቁሰላቸውን የሀገር መከላከያ ሚኒቴር ማረጋጫ ሰጥቷል።
የአልሻባብ አባለቱ ከዶሎ-ሉቅ፣ ከባይደዋ-በርደሌ፣ ከጎዴ-ሁዳር፣ ከሉቅ-ሁከርትና ሌሎች ቦታዎች በ6 ቡድን 59 ፈንጂዎችን በማጥመድና 9 የሞርታር ተኩሶችን በመጠቀም የሠራዊቱን ጉዞ ለማደናቀፍ እንደሞከሩ  ታውቋል።
በሠራዊቱ ከተገደሉት የሽብርተኛ ቡድኑ መካከልም በቀጠናው በፈንጂ አቀነባባሪነት የሚታወቀው ጀብል የተባለ ግለሰብ እንደሚገኝ የጠቆመው ሚኒስቴሩ፤ በጥቃቱ የምስራቅ ኃይል ምድብ የተዋጊ ሄሊኮፕተር ክንፍና የምስራቅ ዕዝ ልዩ ልዩ ክፍሎች ተሳትፈዋል ብሏል።

LEAVE A REPLY