በውጭ ሀገራት ያሉ ኢትዮጵያውያን  ስለ ህዳሴው ግድብ ለተቀሪው ዓለም ለማስረዳት እየሠሩ መሆኑ...

በውጭ ሀገራት ያሉ ኢትዮጵያውያን  ስለ ህዳሴው ግድብ ለተቀሪው ዓለም ለማስረዳት እየሠሩ መሆኑ ተነገረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የኢትዮጵያን አቋም ለተቀረው ዓለም ለማስረዳት ከምንጊዜውም በላቀ እየሠሩ ናቸው ተባለ።

ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ የሀገራችንን አቋም ለተቀረው ዓለም በስፋት እያስረዱ የሚገኙት በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እና በተለያዩ ቋንቋዎች እንደሆነም ተገልጿል።
በመካከለኛው ምስራቅ፣ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ እነዚሁ ወገኖች ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን መሠረት ያደረገው የኢትዮጵያ አቋም በሌሎች እንዲታወቅ ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ነው የተባለው።
የኢትዮጵያ የዲያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሠላማዊት ዳዊት ዛሬ እንደገለጹት እነዚህ ወገኖቻችን ለግድቡ ሥራ በተለያየ መንገድ የገንዘብ አስተዋፅኦም እያደረጉ ከመሆኑ ባሻገር፤ የቦንድ ሽያጭ በሚፈቀድባቸው ሀገራት የሚኖሩት ቦንድ እየገዙ መሆናቸውንም አስረድተዋል።

LEAVE A REPLY