ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፋት 24 ሰዐት ውስጥ በተደረገው 3 ሺኅ 693 የላብራቶሪ ምርመራ 157 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ሚንስትር አስታወቀ።
ይህን ተከትሎ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5 ሺኅ 846 ደርሷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፋት 24 ሰዐታት 5 ሰዎች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ ይህም በሀገራችን በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፈ ሰው ቁጥር 103 መድረሱን ያሳያል።
በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 298 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ እስካሁን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ብዛትም 2ሺኅ 430 እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።