ጠ/ሚ አብይ አህመድ መንግስት ገልብጦ፣ አገር ሊያፈርስ ይችል የነበረ ሴራ በሚገባ አክሽፏል::
የኦሮሞ ፅንፈኞች የአምቦ ልጅ የሆነው ወጣቱ አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን በማስገደል፣ እንደተለመደው አምቦ የአመፁን ሪችት ተኳሽ ሆና መላው የኦሮሞ ህዝብ በአብይ መንግስት ላይ ተነስቶ ይገለብጠዋል” የሚል እቅድ እንደነበራቸው የኦሮሞ የፖለቲካ ተንታኞች ያስረዳሉ::
አብይ መንግስትና ሀገር ለመታደግ ማድረግ ያለበት –
1) የህግ የበላይነት እንዲከበር ወሳኝ እርምጃዎችን መውሰድ
2) የሃጫሉ የግድያ ወንጀል በአጭር ጊዜ መርምሮ ውጤቱን ለህዝብ ማሳወቅ (የዘገየ ፍትህ እንደቀረ ይቆጠራል! Justice delayed is justice denied!)፣
3) ህግ-አስከባሪው ኃይል ሥርዓት አልበኞች በኦሮሚያ ክልል በሚኖሩ ዜጎች ላይ አደጋ ሲያደርሱ ፊቱን አዙሮ መቆም ሳይሆን ተገቢውን ህግ የማስከበር፣ ዜጎችን ለመታደግ እርምጃ እንዲወስድ ጥብቅ ትእዛዝ ማስተላለፍ፣
4) የአዲስ አበባ ኗሪ ህዝብ ከመንጋ ወረራና ጥቃት ራሱን እንዲከላከል ያስቻለውን የባልደራስ መሪ እስክንድር ነጋን ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ ከእስር መፍታት (ይህ ካልሆነ የአዲስ አበባ ህዝብ “መከታ ጋሻዬ” የሚለውን እስክንድር ነጋን ለማስፈታት የተለያዩ ህዝባዊ ተቃውሞችን ማካሄድ:: በዳያስፖራው ያለው ዜጋም እስክንድርን ማሰር በአዲስ አበባ ህዝብ ላይ የተቃጣ አደጋ መሆኑን ተገንዝቦ፣ እስክንድር እንዲፈታ ትግሉን ማጧጧፍ ይኖርበታል)፥፥ አብይ እስክንድርን ይሁን ባልደራስን ማየት ያለበት እንደ አጋር እንጂ እንደ ባላንጣ ፈፅሞ መሆን የለበትም፥፥ (PM Abiy Ahmed’s Achille’s heel is his unbridled attack on Balderas, a non-violent pro-Ethiopian unity force founded by the remarkable Eskinder Nega. Abiy should correct his weakness).
አብይ እስካሁን ድረስ ተከላካይ ሁነህ ዘልቀሃል:: ከአሁን በኋላ ግን መንግስትህ ሊቆምና ሀገርም ልትረጋጋ የምትችለው ተከላካይነትህን ወደ አጥቂነት ካሸጋገርክ ብቻ ነው:: መሪነቱን ፈልገኸው የነብር ጅራት ይዘሃል:: ከያዝከው ደግሞ እንኳን መልቀቅ፣ ላላ አርገህ ብትይዘው በህይወትህ ላይ አደጋ መጋበዝ ነው:: ያ ደግሞ እንዲሆን አንተ ላይ ተስፋ ያሳደረው የኢትዮጵያ ህዝብ ፈፅሞ አይፈልግም::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ከክፉ ሰዎች ይጠብቅልን!