የባሕር ማዶ ደብዳቤ ቁጥር 6 || ሰማነህ ጀመረ (ከካናዳ)

የባሕር ማዶ ደብዳቤ ቁጥር 6 || ሰማነህ ጀመረ (ከካናዳ)

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ፤ አሰላለፍህን ታሳምር ዘንድ ጥሪየ ይድረስህ፤

ውዱና ጎስቋላው ወገኔ ሆይ። በሃሳብና በጭንቀት የታጀበው ሰላምታየ ከባህር ማዶ ይድረስህ። እኔ ከሃገሬ ከወጣሁ ብዙ ጊዜ ሆኗል። በየጊዜው ወደ ሃገር ቤት እየመጣሁ ኑሮህንና ስቃይህን ሁልጊዜ አያለሁ። ኑሮህንና ሕይወትህን ለመለወጥ የምታደርገውን ውጣ ውረድ አይቸ ብዙ ተስፋ ጥየብሃለሁ። ይህን ጥረትህን ሊአጨልሙብህ የሚሯሯጡና መሰናክል የሆኑብህ ሃገር በቀል አሜኪላዎች እንደሚአስቸግሩህም  በጽኑ አውቃለሁ። እኔ እንደሆንሁ ኢትዮጵያዊነቴን ለውጨ የውጭ ዜግነት ከወሰድሁ ድፍን ሃያ ሁለት ዓመት ሆኖኛል። የቅንጦት ኑሮን ለመኖር፤ እንደ ድመት ምቾቴንና ሰላሜን ከመፈለጌ የተነሳ ክረምት በረዶ እየጠረግሁ፤ በጋ ሙቀት እየተቃጠልሁ እኖራለሁ። ምቾት ቢኖረኝም ውስጣዊ ሰላም የለኝም።

ሰላሜ የሚረበሸው ያንተን ጉስቁልናና ስቃይ ሳስብ ነው። በውጭ የጥድፊያ ኑሮ ላይ ሆኘ ያንተንና የሃገሬን ሁኔታ ሳላስብና ሳላምጥ የዋልሁበትና የተኛሁበት ጊዜ አይታወሰኝም። በአካል ካንተ ጋር ባልሆንም ሁልጊዜ አስብሃለሁ፤ እጨነቅልህአለሁምከአስር ሽህ ኪሎሜትር ርቀት ላይ ሆኘ ስትደሰት እደስታለሁ፤ ስታዝን አዝናለሁ፤ ስታስብ አስባለሁ ስትከፋ እከፋለሁ-ኧረስንቱ። በውጭ በኖርሁበት ጊዜ በአንተና በኢትዮጵያ ሃገሬ ላይ ደባና ሴራ ሰርቻለሁ ብየ አላምንም። ሳላውቅ ጎድቸህ፤ ወይም አስቀይሜህ ከሆነ ከስርህ ወድቄ ይቅርታህን እጠይቃለሁይቅር ባትለኝም እረዳለሁና አታስብ። ድፍረት አይሁንብኝ እና ትንሽ ምክሬን እንዳጋራህ ግን ፍቀድልኝ።

በቅርቡ ከሃጫሉ ሞት በሗላ ዘረኞች፤ ጽንፈኞች፤ የስልጣን ጥመኞች፤ ተገንጣዮችና አክራሪዎች ያደረሱብህን ሰቆቃና ስቃይ ሰምቸና አይቼ በእጅጉ አዝኛለሁ። ስሜቴ ተጎድቷል።እንዴት እንደምረዳህ ባላውቀውም በፀሎቴ ሁሌም አስብሃለሁ። ሶሪያን፤ አፈሃኒስታንን፤ ኢራክን፤ የመንን ያየሁ ስለሆነ የነዚህ ሃገራትሕዝብን እጣ ፈንታ እንዲደርስህ አልመኝም። ስለሆነም እራስህን ከልቂት፤ አገርህን ከውድመት ለማዳን እንድትሠራ ጥሪየን በምክር መልክ አቀርባለሁ። የፖለቲካ፤ የሃሳብና የሃይማኖት ልዩነት በመካከልህ እንዳለ አውቃለሁ። ልዩነት መኖሩ የሚጠበቅ ነው። ልዩነት የለውጥ መሰረት ነውና። ልዩነትህ ግን ሕዝብ ለማጥፋት ሃገር ለመበተን የሚዳርግ አይሁን ይህን ያልሁት በምክንያት ነው። አሁን ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ምስክር ሆኖኛልስለሆነም ሰከን ብለህ አስበውና በፍጥነት ተገዳደረው። የፖለቲካና የአስተሳሰብ ልዩነቶች ከሃገር በላይ እንዲሆኑ አትፍቀድ።

እንደምታውቀው ኢትዮጵያ በጠላት ከመወረሯ በፊት መሳፍንቱ፤ መኳንንቱ፤ የሃይማኖት አባቶች፤ ፖለቲከኞችና የጦር አበጋዞች በፖለቲካ፤ አስተዳደርና ሥልጣን ምክንያት ውስጣዊ ሽኩቻቸው የተጧጧፈ ነበር። የልዩነታቸው መሰረት ስልጣንና በተረ-መንግሥት ነበር። በከረረ የስልጣን ሽኩቻ እና በእርስ በርስ መጠፋፋት ተጠምደው በነበረበት ወቅት ነበር ፋሽስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን የወረረው።

ታሪክህ እንደሚነግረን መኳንንቱ፤ ባለስልጣኑና አንተ መካከላችሁ የነበረውን ግብግብ ገሽ አርጋችሁ ምታ ነጋሪት፤ ክተት ሰራዊት በሚል እንደ አንድ ሰው ቆመእንደ አንድ ልብ መክረ ረ ፋሽስት ዘመቻእንዳደረግህ ዓለም መስክሮልሃል። ሕብረትህና አንድነትህ ፍሬ አፍርቶ ጠላትአሸንፈ በመጣበት መልሰሃል ለሃገርህ ነፃነራስህክብርንና ማንነትን አጎናጽፈሃልብር ለአንተ ይሁንፋሽስት ተሸንፎ ከተባረረየሃገር ሉላዊነት ከተከበረ በኋላ ባለስልጣኖችህና የጦር አበጋዞችህ የስልጣን ሽኩቻቸውንእንደገና ቢቀጥጠባቸው ከሃገር ጥቅም በታች እንደሆነ ግን የተረዱ ነበሩ

ውዱ ወገኔ ሆይ

ይህ ዓይነቱ ሁኔታ ባንተና በኢትዮጵያ ብቻ የተጀመረና የሆነ ይመልህ። የሌላ ዓለም ሃገራት ሉዓላዊነታቸውን የሚፈትን ሁኔታ ሲገጥማቸው መንግሥትና ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች በመካከን ተቃርኖ በይደር አቆይተው ጠላታቸውን በተባበረ ክንድ ተዋግተው አሸንፈዋል። የሃገሉዓላዊነት አስከብረዋል። ቻይና ለዚህ ድንቅ ምሳሌ ትሆናለች። የኮሚንታንግ መንግሥትና የማኦ ሴቱንግ የኮምኒስት ድርጅት ከፍተኛ በሆነ ውስጣዊ ጦርነት ውስጥ ነበሩ። ጦርነቱ በአድሃሪና በተራማጅ ኮምኒስቶች መካከል የነበረ የስልጣን እና የርዕዮተ ዓለም ሽኩቻ ነበር። በዚህ ግብግብ ብዙ ሕዝብ አልቋል፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተፈናቅለዋል፤ አካለ ጎደሎ ሆነዋል፤  ሰፊ ንብረት ወድሟል። ቻይና በዚህ ሁኔታ ላይ እያለች ጃፓን ኢምፔሪያሊዝም በመወረሯ የሃገሪቱ ሉላዊነት አደጋ ላይ ወደቀ

በዚህ ጊዜ የሻንግ ሃይሸክ መንግስትና የማኦ ሴቱንግ ኮምኒስት ጽያን የተኩስ አቁም ስምምነት አድረገው ጋር ጠላታ በሆነው የጃፓን ኢምፔሪያሊዝም ላይ በጋር ዘመቱ። በአጭር ጊዜ ጠላትን አሸንፈው ሉላዊነታቸውን አስከበሩ። በዚህ ጊዜ የሻንግ ሃይሸክና የማኦ ደጋፊ የነበረው ቻይናዊ ሁሉ አሰላለፉን አሳምሮ ከጎናቸው በመቆም ወራሪውን ሃይል እንዲአሸንፉ በብቃት እረድቷል። ቁጥራቸው የበዛ ከሃዲዎችና ባንዳዎች በመኖራቸው ቻይናን ብዙ ዋጋ አስክፈለዋታል።

እዚህ ላይ ባዕዳን ሃገራት ጀግንነት አረያነትህን እንዴት እንደሚጠቀሱ ላስታውስህ ወደድሁ። ማኦ ሴትንግ የፀረ ጃፓን ውጊያውን ሲአደርግ ሠሪዊቱን የሚቀሰቅሰው ጀግንነትን ከኢትዮጵያ የነፃነት ታጋዮች እንዲማሩ ታሪክን በማጣቀስ ሰራዊታቸውን ለውጊያ ያነቃቁ ነበር። በኮሪያ ጦርነት ጊዜ የቃኘው ጦር ባሳየው ወደር የሌለው ጀግንነት በኮሪያኖችና ና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሁሌ ወደስና በዓርያነት ሲጠቀስ ኖሯል። ታያ ሌሎች ሃገራት እንዲህ የሚአወድሱህ ሕዝብ ሆነህ እያለ ለእናት ሃገርህና ወገንህ መከታ የማትሆንበት ምክንያት ሊኖር አይገባም

በ1966 ዓ.ም. የኢትዮጵያ አብዮት ሲጀመር ከፍተኛ የሆነ የርዮተ ዓለምና የስልጣን ፍጊያ በሶስት ግንባር ተካሂዷል። አንድኛ ፍልሚያ የኢትዮጵያ መንግትና ሕዝብ በአንድ በኩል ሃገር ገንጣይ አስገንጣይ በተቃራኒ ሆነው ተፋልመዋል። ለተ የማኦሴቱንግና ኤንቨር ሆሽካ ርዕዮተ ዓለም በሚከተሉ ድርጅቶችና በደርግ መንግመካከለ የነበረው ጦርነት ነበር። ሶስተኛው ዘርፍ ደግሞ በግራ ዘመም የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የርዕዮተዓለም ሳይሆን ስልት ልዩነት እና ለስልጣን ባለቤትነት የተደረገ የርስ በርስ ፍጅት እንደሆነ ይታወሳልልዩነቶች ሲጨመቁ ግን አገር በማስጠበቅና የመንግስት ስልጣን ባለቤት ለመሆን የሚደረግ ፍልሚያ እንደነበር ግልፅ ነው

ሃገር ከውስጥ እየደማች በነበረበት አስቸጋሪ ወቅት ነበር ሶማሊያ ሉዓላዊ ሃገራችንን ፍራ የወረረችውየኢትዮጵያ ሕዝብም አባ የሞተለት እና ይለቀሳልእናየሞተችለት በህ ይለቀሳል እህ የሞተችለት ወንድይለቀሳልወንድም የሞተለት ባአ ይለቀሳል፤ ሃገርየሞተለት ወዴት ይደረሳል እያለ በማንጎራጎር ብሎ በአንድነት ዘመተ። ሕዝባችን ልክ በፋሽስት ኢጣልያ ላይ እንዳደረገው ወገናዊ አሰላለፉን በማሳማር የሶማሊያን ወራሪ ድባቅ መትቶ ነፃነቱን አስከብሯል በኢትዮጵያ ምድር ታሪክ ራሷን የደገመችበት የጀግንነትህ ክስተት ሆኖ ስናስታውሰው ይኖራል

በዚህ መሃል አሰላለፋቸውን ከጠላት ጋር ያደረጉ ሃገር ከሃዲዎች፤ ወገን አስጨፍጫፊዎች፤ የእናት ጡት ነካሾችና ባንዳዎች ነበሩ-ዛሬም አሉ። ወገን መስለው የወገንን ቋንቋ እየተናገሩ፤ ከወገን ጋር እየፀለዩ፤ አብረው እየበሉ እየጠጡ፤ በውስጣችን አድረው ብዙ ያስጠቁን፤ ሃገርና ወገንን ዋጋ ያስከፈሉ ትቂቶች አልነበሩም፤ አሁንም አሉ።  

ከሰሞኑ ሃጫሉ በከሃዲዎች፤ በሃገር ገንጣዮች፤ ባንዳዎች፤ የሃይማኖትና የጎሳ ጽንፈኞች በአሳዛኝ ሁኔታ ተገሏል።  ህን እኩይ ግባር የፈጸሙት ቡድኖች፤ ግለሰቦች፤ ተገንጣዮችና ባንዳዎች የነበራቸው ዓላማ ግልጽ ነው። ለ30ዓመታት ሕገ መንግስት ቀርው የኢትዮጵያን ሕዝብ በጎሳ፤ በጎ፤ በሃይማኖት ነጣጥለው እርስ በርስ በማባላት ወደ ስልጣን ኮርቻ እንደገና ለመመለስ የጠነሰሱት ሴራ ነው።

ይህን አስቀያሚ ተግባር የፈጸሙበት ወቅት ስናስበው ደግሞ ይበልጥ ያመናልየሕዳሴ ግድባችንን ውሃ ሙት በተመለከ ከቀንደኛ ጠላታችን ግብ ጋር በተባሩት መንግስታት የጥታው ምክር ቤት፤ በአፍሪካ እና አውሮፓ ህብረቶች አማካይነት ወይይትና ድርድር በምናደርገብት ወቅት መሆኑ ስናስበው ይበልጥ ያሳዝናል። የድርድሩን አቅጣቻ ለማስቀየር ወይም ግብ አሸናፊ ሆና እንድትወጣ የተደረግ ሙከራም በመሆኑ ገዳዮችና አስገዳዮች ከሃገር ከሃዲነት ተርታ ያስፈርጃቸዋል። የነኝህ ግለሰቦች፤ ቡድኖችና ፖለቲከኞች ዓላማ በግርግር ስልጣን መያዝ፤ ካልተቻለ ኢትዮጵያን ለመበተን የጠነሰሱት ሴራ መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ ልትገነዘበው ይገባል።

ግድቡ ሲጠናቀቅ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚና ልማት ሊሰጥ የሚችለው ፋይዳ ከፍተኛነት የሚአጠያይቅ አይሆንም።ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ግድቡ በሙሉ አቅሙ ሲሰራ በዓመት እስከ ሶስት ቢልዮን ዶላር ገቢ እንደሚአስገኝ ይታመናል። ይህም የሃገራችንን ጠቅላል ዓመታዊ በጀት ግማሹን ማለት ነው። ግድቡ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ስለሚፈጥር ለስራሕዝብ  ሰፊ የስራ ድል ይፈጥራልይህን በመሰለ የሃገርና የሕዝብ ተቋም ላይ ደባና ጥፋት የሚአደርሱ ሁሉ ሃገር ከሃዲ ተብለው ሊፈጁ ይገባል። በሃገር ክህደት ወንጀል ተከሰው የማያዳግምና አስተማሪ የሆነ ቅጣት እንዲወሰንባቸው ኢትዮጵያዊያን መጠየቅ አለባቸው። ሃገር ክህደት ከወንጀሎች ሁሉ የከፋው ውንጀል ስለሆነ ፍትሕ የሚደረገው በሽምግልና ባለመሆኑ ተገቢውንና የማያዳግም ሕጋዊ ቅጣት መጣልና መፈጸም ለነገ የሚባል መሆን የለበትም።

ንም ሰው ወላጅ፤ ዘር፤ አካባቢ፤ ጎሣ፤ አገርና ሃይማኖትመርጦ አልተወለደም የተፈጥሮ ሕግ ሆኖ ሁላችንም የሁለት ተቃራኒ ታዎች ባደረጉት ግንኙነት ተፈጥረናል። ይህ የሆነው ሃገር በምንላት ኢትዮጵያ ቤት ውስጥ ተፈጥረን ተባዝተን ተገኝተናል። የጋራ መኖሪያችንና ዞሮ መግቢያችን ኢትዮጵያ ነች። ይህችን የጋራ ቤታችንን የሚረብሿትንና ቢቻላቸው ሊወድሟት የሚራወጡትን ሁሉ ፋሽትንና የሶማሊያ ተስፋፊዎችን በጋ እንዳሸፍናቸው ሁሉ በጋር ቆመን ን ለማዳን መስራት አለብን። ገር የሚፈርሰውና የሚወድመው በትቂት ወንበዴዎች፤ ባንዳዎች፤ ከሃዲዎችና ጽንፈኞች ሳይሆን በሐቀ ብዙሐን ዝምታና ቸልተኝነት መሆኑን መዘንጋት አይኖርብንም።

ጠቅላይ ሚንስትር /ር ዓብይ የኢትዮጵያ መሪ ከሆኑ ሁለት ዓመት አልፏቸዋል። የተበላሸ አመራር፤ በጎሳ፤ በጎጥና በሃይማኖት የተበጣጠሰች ኢትዮጵያ፤የላሸቀና የደቀቀ ኢኮኖሚ፤ ብልሹ መስተዳድርና ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስራአጥ ትውልድ ያላት ሃገር ከኅወሃት/ኢሕአዴግ ተረክበዋል። በፖለቲካ ድርጅቶች፤ በክልሎች፤ በሃማኖቶች፤  በደህንነቱና በሠራዊቱ መካከል በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ ሽኩቻ ያለባት ሃገር ተረክበዋል። ፈተናው ብዙ፤ መንገዱ ጠመዝማዛ፤ ግቡ በጣም ሩቅ የሆነ ሁኔታ የገጠማቸው መሆኑን ሁሉም ይረዳዋል።

ይሁን እና በዚህ ሁለት ዓመት ብዙ ጥሩ ስራዎችን አሳይተውናል። ቢሆንም ግድፈቶች የሉባቸውም ማለት ግን አይደለም። ምንም ይሁን ምን መንግሥታቸው ሃገን ለውድቀት የሚዳር ግን አይመስልም ስለሆነም ሁላችንም በአገር ላይ የመጣውን አደጋ ሰከንባለ አምሮ ከምንመረምርበትና ሕዝባዊ አሰላለፋችንን ከምንፈትሽበትአስራአንደኛው ስዓት ላይ መድረሳችንን መረዳት ያስፈልገናል። ስለዚህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ጥቃቅን ልዩነቶችን ገሸሽ አድርገህ አሰላፍህን አሳምር ከዶክተር ዓብይ ጎን ተሰልፈህ ኢትዮጵያህን አድን። ሌላው ገር ካደረችበኋላ ይደረስበታል። እኔም ባይ አለሁ!!

ቀን፤ ሐምሌ 2, 2012

LEAVE A REPLY