ህወሓት በነሀሴ ወር ለሚያካሂደው ክልላዊ ምርጫ ምርጫ አስፈጻሚ ኮሚሽነሮችን ሾመ

ህወሓት በነሀሴ ወር ለሚያካሂደው ክልላዊ ምርጫ ምርጫ አስፈጻሚ ኮሚሽነሮችን ሾመ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ቀጣዮንና ስድስተኛውን ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ የወሰነው ህወሓት ዛሬ ባካሄደው የትግራይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚሽነሮችን መርጧል።

ምክር ቤቱ ምርጫውን ያስፈጽሙልኛል በሚል አምስት ግለሰቦች የሾመ ሲሆን፤ በዚህም  መሠረት አቶ ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም፣ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር፣ ወይዘሮ ጽጌሬዳ ዲበኩሉ ደግሞ ምክትል ኮሚሽነር መሆናቸው ይፋ ሆኗል።
በተያያዘም አቶ መረሳ ፀሐየ፣ አቶ መሀመድ ስዒድ ሀጎስና ዶክተር ጸጋ ብርሃነ ደግሞ፣ የኮሚሽኑ የሥራ አመራር በመሆን መመረጣቸው ተሰምቷል።
ከአንድ ወር በኋላ በትግራይ በሚካሄደው ክልላዊ ምርጫ፤ ትግራይን በአምባገነንነት እያስተዳደረ የማገኘው  ህወሐት  በክልሉ  ተፎካካሪ ፓርቲዎች እንደሚንቀሳቀሱ ለማሳየት የፈበረካቸው እንደ “ባይቶና”፣ “ሳልሳይ ወያኔ”፣ “የትግራይ ብሔራዊ ሸንጎ” ን ዓይነት ተለጣፊ ፓርታዎች ጋር  የይስሙላ ፉክክር ለማድረግ እየተዘጋጀ መሆኑ እየተየገረ ነው።
በአንጻሩ በትግራይ ክልል ከፍተኛ ድጋፍ ያላቸውና ህወሓት በጠላትነት የፈረጃቸው አረና ትግራይና በዶ/ር አረጋዊ በርሄ የሚመራው ትዴት ፓርቲዎች የሚደረገው ምርጫ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዕውቅና የሌለው በመሆኑ አንሳተፍም ብለዋል።
በወ/ት ብርቱኳን ሚዴቅሳ የሚመራው ምርጫ ቦርድ ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ በኮቪድ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም መወሰኑን ቢገልጽም፤ ህወሓት ግን በሚያስተዳድረው የትግራይ ክልል፤ ክልሉ የራሱን ኮሚሽን ለማቋቋም ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።
በዚህም መሠረት ከባለፈው ሳምንት ቅዳሜ እስከ ማክሰኞ ድረስ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የኮሚሽኑ አባላት ይሆናሉ የተባሉ ሰዎች ሲጠቆሙ ቆይተው የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚሽነሮቹ ሹመት ዛሬ ተከናውኗል።
በቅድሚያ 776 ሰዎች ተጠቁመው እንደነበር እና ከእነርሱ መካከልም በትናንትናው እለት ከክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋር ሦስት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች በተቀመጡበት ዐሥር ግለሰቦችን ለኮሚሽነሩ የቦርድ አባልነት በእጩነት መርጠው አቅርበው እንደነበርም ታውቋል።
የተመረጡት ሰዎች በመቀለ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን፣ የታሪክና ሕግ ምሁራን መሆናቸው እየተነገረ ይገኛል።

LEAVE A REPLY