ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ5 ሺኅ ሄክተር በላይ የሚሆን መሬት በዘር ለመሸፈን ማቀዱን አስታወቀ።
በከተማው ያሉ 5 ሺኅ አርሶ አደሮች ከ4 500 ሄክታር በላይ መሬት ለመኸር ምርት እንዳዘጋጁ የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽነር ወ/ሮ ፈቲያ መሐመድ መንግሥት ለእነዚህ አርሶ አደሮች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
ስንዴና ጤፍ በመኸር ወቅት ለመዝራት የተዘጋጁ የሰብል ዓይነቶች ሲሆኑ፣ ከዚህ በተጨማሪ በከተማ ግብርና በ650 ሄክታር መሬት ላይ አትክልት ለማልማት ቅድመ ዝግጅት የተደረገ መሆኑን ሰሠምተናል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለከተማ አርሶ አደሮች በዚህ መልክ ለግብርና ሥራ የሚውለው ይህ ቦታ በትምህርት ቤቶች፣ በመንግሥት ተቋማት፣ በግል ድርጅቶችና ለረዥም ዓመታት ያለ ጥቅም ታጥረው በቆዩ ሥፍራዎች የሚገኝ መሆኑ ታውቋል።