በዓይነቱ ልዮ የሆነ የቱሪዝም የታክሲ አገልግሎት በአዲስ አበባ ሥራ ሊጀምር ነው ተባለ

በዓይነቱ ልዮ የሆነ የቱሪዝም የታክሲ አገልግሎት በአዲስ አበባ ሥራ ሊጀምር ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአዲስ አበባ ከተማ ለቱሪዝም አገልግሎት የሚውል በዓይነቱ ልዮ የሆነ ታክሲ ወደ ሥራ ሊገባ ነው መሆኑ ተነገረ።

ታክሲዎቹ ወደ ሃገር ቤት የሚገቡት መንግሥት በፈቀደው ከቀረጥ ነፃ እድል መሆኑን እና እስካሁንም በቁጥር አነስተኛ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ገብተዋል መባሉን ሰምተናል፡፡
የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶ/ር ሒሩት ካሳው ከካምፓኒዎች ጋር በጉዳዮ ላይ በተደረገው ጥልቅ ውይይት ላይ  ታክሲዎቹ ከቀረጥ ነፃ በሆነው ፈቃድ ከሕጉ ውጭ ሢሠሩ ከተገኙ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል።
 ለነዚሁ አሽከርካሪዎች የሀገሪቱን እና የቱሪዝም መዳረሻዎችን አስመልክቶ  የአቀባበል እና የቋንቋ ስልጠና እሰጣለሁ  እንደሚሰጥም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
እንዲህ ዓይነቱን አዲስ አሠራር  እሠራለሁ ብሎ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር የተፈራረመው ድርጅት 250 የታክሲ አሽከርካሪ ግለሰቦች አሮጌ መኪናዎችን እንደቅድመ ክፍያ ዋጋ ተቀብሎ አዲስ መኪና ለመስጠት ተስማምቷል።
ተሽከርካሪዎቹ ባለሠባት መቀመጫና ስሪታቸው የቻይና መሆኑን የጠቆመው ዜና፤ ካምፓኒዎቹ ቅድሚያ 172 ሺኅ ብር በመጠየቅ አገልግሎቱን እንደሚሰጡ ከመጠቆሙ ባሻገር፤  ቀሪው ክፍያም በ5 ዓመት ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ መሆኑን ገልጿል።
በአዲሱ የቱሪዝም የታክሲ አገሌግሎት ላይ ለረጅም ጊዜ በታክሲ ሥራ ሕዝቡን ሲያገለግሉ ለቆዩ ቅድሚያ የሚሰጥ ሲሆን፤ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሒሩት ካሳው ዛሬ ከኩባንያዎቹ ጋር የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም እቅዱን እውን አድርገዋል።

LEAVE A REPLY