የኦሮሞ ሕዝብ ከመከፋፈል አባዜ እንዲወጣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሳሰቡ

የኦሮሞ ሕዝብ ከመከፋፈል አባዜ እንዲወጣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሳሰቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  የኦሮሞ ህዝብ አንድነቱን አጠናክሮ ወደ ቀድሞው የማንነቱ እሴቶቹ መመለስ እንደሚኖርበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

አሁን ካለው የመለያየትና ኦሮሞን ከመከፋፈል አባዜ ወጥቶ የኦሮሞ ህዝብ ቀድሞ የሚታወቅባቸውን እንደ ጉዲፈቻ፣ ዐቃፊነት እና ሰውን ወዳድነት፣ እንዲሁም ባዳን ዘመድ የማድረግ እሴቶቹን ይበልጥ በማጠናከር የተጀመረውን ለውጥ ለማሻገር በጠንካራ መንፈስ መሥራት እንደሚኖርበትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ባለፉት ሥርዓቶች የኦሮሞ ህዝብ ጥላቻ እና መገፋት ደርሶበታል ማለተታቸውን ያስነበበው የብልፅግና ፓርቲ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ይህን መገፋትና ማግለል በሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ላይ ለመድገም ማሰብ አይገባም ማለታቸውንም ገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኦቢኤን ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ዋቢ ያደረገው መረጃ፤ “ሁሉም ከውሸት፣ ከቅናትና ከሌብንት በመውጣት ህዝቡን በቅንነት ማገልገል ይጠበቅበታል። የኦሮሞ ህዝብ የቀድሞ የማንነቱን ተግባራዊ በማድረግ ከሌሎች ብሄር ብሔረሰቦች ጋር በፍቅር፣ በአንድነት እና በመተባበር መቆም ከቻለ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን የማድረጉ ጉዞ እሩቅ አይሆንም ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መናገራቸውንም ዘግቧል።

LEAVE A REPLY