ከድኅረ ኮሮና በኋላ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸዉን በተለያየ መደብ ተከፍለው ይጀምራሉ ተባለ

ከድኅረ ኮሮና በኋላ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸዉን በተለያየ መደብ ተከፍለው ይጀምራሉ ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ (ከድኅረ ኮሮና) በኋላ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸዉን የሚጀምሩት በተለያየ  መደብ ተከፍለዉ እንደሆነ ተነገረ።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደ ማሪያም ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ የ2012 የትምህርት ዘመን ማካካሻና ማሟያ  ትምሀርትን ለመስጠት ተቋማት እየሠሩ መሆናቸውን ጠቁመው፤በዚህ መሠረት ከትምህርት አሰጣጥ እስከ ቅበላ የተለያዩ መርሀ ግብሮች እንደተዘጋጁ አስረድተዋል።
በኮሮና ምክንያት ያለፈውን ትምህርት ለማካካስ የትምህርት አሰጣጡ ሳምንቱን ሙሉ እስከ ምሽት የሚከናወን መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሯ፤ ከአራተኛ ዓመት በላይ ያሉና ተመራቂ ተማሪዎች በቅድሚያ እንዲገቡ፣ ትምህርታቸዉም በኦንላይንና በገፅ ለገፅ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይደረጋል ብለዋል።
በአንጻሩ አስቀድመው ወደ ትምህርት የገቡት መርሀ ግብራቸውን እንዳጠናቀቁ ከሦስተኛ ዓመትና ከዚያ በታች ያሉት ተማሪዎች በተመሳሳይ መንገድ ትምህርታቸዉን እንዲከታተሉ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን ሰምተናል።
በአዲስ መልክ የተነደፈው የከፍተኛ ትምህርትም ሆነ አጠቃላይ ትምህርቱ ገፅ ለገፅ (መደበኛ ትምህርት አሰጣጥ) ተግባራዊ የሚሆነው የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ   ስጋት መሆኑ መቀነሱ በጤና ሚኒስትርና በመንግሥት ሲረጋገጥ ብቻ መሆኑም ይፋ ተደርጓል።

LEAVE A REPLY