መክሸፍ እንደኦሮሚያ፤ የከሸፈ ክልል እና የምስኪኖች ሰቆቃ
ተtክለሚካኤል አበበ፤ ቶሮንቶ፤ ካናዳ፤ ሀምሌ፤ 2012/2020
እንደመግቢያ፤ “ነፍጠኛው ተነሳ፤ ሞቶ፤ ርቆ ከተቀበረበት፤”
ይህ ጽሁፍ፤ ቀደም ሲል የነገሌ አርሲው ተወላጅ፤ ወንደወሰን ተሾመ ከጻፈው ጽሁፍ የቀጠለና በዘዚያ ጽሁፍ የተነሳሳ ነው፡፡
የሀጫሉን ሞት ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች የደረሰውን ጥፋት ሳስብ፤ በእውኑ የኦሮሚያ መንግስት፤ ክልል መምራት ይችላል ወይንስ ከሸፈ የሚል ጥያቄና ክርክር አጭሮብኛል፡፡ የኦሮሞ ልሂቃን፤ ክልል አሉ፤ ክልል አገኙ፡፡ ቋንቋ አሉ፤ እሱንም አገኙ፡፡
በአገራችን፤ አባቶቻችንና እናቶቻችን በገነቡት አገር ላይ ባይተዋርና ባእዶች ተደረግን፡፡ በቱርጁማን መኖርን፤ በአስተርጓሚ መነገድን፤ መዳኘትን ለመድን፡፡ እንደሚባለው፤ አያት ቅድመአያቶቻችን፤ ሰፋሪዎች፤ ቅኝ ገዢዎች፤ ጡት ቆራጮች ቢሆኑ እንኳን፤ በእውኑ እኛ የአያቶቻችን የልጅ ልጆች የምንሳደድበት አመክንዮም ሞራልም እንደሌለ ጠፍቶን አይደለም፡፡ ግን ይሁን አልን፡፡ ተሸንፈን፤ ይሄን ብለንም ግን፤ ነፍጠኛውን ላይመለስ አርቀን ቀብረነዋል ካሉን፤ ከ30 አመታት በኋላም ያፈራነው፤ ክልላቸውን በሀላፊነትና በብቃት የሚመሩ መሪዎችን ሳይሆን፤ ዜጎችን የሚገድሉ፤ የሚያስገድሉ፤ ንብረት የሚያቃጥሉ፤ የሚያስቃጥሉ፤ ሽብርተኞችን ነው፡፡ ጀግኖችን አይደለም፡፡ በኦሮሚያ ውስጥ ለደረሰው ጥፋት፤ የፌደራሉም የክልሉም መንግስት ተጠያቂዎች ናቸው፡፡
ካለፈው ስንቀጥል፤
ኦሮሞ ደግ፤ ቅን፤ በጦርነት እንኳን የማረካቸውን እንደልጅ የሚያሳድግ እንደ ሚስት የሚጠብቅ፤ አደንና ግድያ ለይቶ የሚያውቅ ህዝብ ነው፡፡ ኦሮሞ፤ ጫካ እንጂ ከተማ አደን አይወጣም፡፡ ኦሮሞ ሰው ዘቅዝቆ የሚሰቅልም አይደለም፡፡ እነዚህ ነገሌና ሌሎች የኦሮሚያ ከተሞ ውስጥ፤ ሰው በገጀራ የቆራረጡ፤ ሰው ዝቅዝቀው የሰቀሉና ከግዳያቸው አጠገብ ፎቶ የሚነሱ ሰዎች፤ ይሄን ሰው ማረድና መቆራረጥ ከየት አመጡት? የኢትዮጵያ ባህል ነው እንዴ? ልብወለድ አምነው፤ ጡት በመቁረጥና በመስለብ በሚያሙት ንጉስ “ምኒሊክ” ለተቆረጡ ጡቶች፤ የአኖሌ ሀውልት መታሰቢያ ያቆሙ ሰዎች፤ ባለፈው ሰኔ 23 ያደረጉት የሚወገዝ ድርጊት ነው፡፡
ሰው እንዴት ከ150 በፊት ተፈጸመ የተባለን ልብወለድ እያመነዠከ፤ በ21ኛው ክ/ዘ፤ ከዚያ የከፋ ግፍ ይፈጽማል? ሰው እንዴት፤ አርሲ ነገሌ ከተማን የገነቡ፤ ለዚህች ከተማ እድገት መስዋእትነት የከፈሉ፤ አረቄ አውጥተው፤ ከብት አደልበው፤ እርሻ አርሰው ይህቺን ከተማና አገር የገነቡ፤ እኛና፤ ወንድም እህቶቻችንን ያስተማሩ፤ ለትምህርት እድገት አስተዋጽኦ ያደረጉ ሰዎች ንብረት ያወድማል?
ባለፈው እንደተገለጸው፤ የነገሌ አርሲ የረጅም ግዜ ነዋሪው፤ አቶ ፈቃደ ደጀኔ፤ ባንድ ወገን ኦሮሞ ነው፡፡ አማራ ኦሮሞ ሳይል፤ ከ40 አመታት በላይ ትውልድ ያሰተማረና፤ ባለፈው አመት በበጎ ሰው ሽልማት የታጨ ሰው ነው፡፡ የዛሬ አመት ከ7 ወር፤ ህዳር 2010 ላይ፤ ማቃጠል የጀመሩትን ትምህርትቤት፤ በዚህኛው ዙር ጨረሱት፡፡ ሕዳር 2010 የተቃጠሉት ላብራቶሪና መዝገብ ቤቶች ነበሩ፡፡ በወቅቱ፤ የአካባቢው ሕዝብ ቃጠሎውን ሊያጠፋ ሲሞክር፤ የከተማው ፖሊሶች ሕዝቡን እሳቱን እንዳያጠፋ ያባርሩ እንደነበር ማስረጃ አለ፡፡ በኋላም፤ በምርመራው ወቅት፤ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ፤ አንዳንድ ፖሊሶች፤ “ለምን የተቀረውንስ አልጨረሳችሁትም”
እንዳሉ ማስረጃ አለን፡፡ ሰው እንዴት ትምህርት ቤትና ክሊኒክ፤ ያቃጥላል? መንግስት ያኔ ያልቀጣቸው፤ እንደውም ለማባበል የሾማቸው፤ ኦሮሞ ያልሆኑ ኦሮሞዎች ናቸው እነሆ ዛሬ ይሄንን ይፈጸሙት፡፡
እንደተባለው፤ እንደተመኙት፤ ነፍጠኛም ይሁን የተቀረው ሕዝብ ከተማዎቹን ጥሎ ቢወጣ እኮ፤ ጅልነት እንጂ፤ ሕንጻውና ተቋማቱ ቢተርፉ ለቀሪው የኦሮሞ ሕዝብ እድገት ያስፈልጋሉ፡፡ ጉዳዩ ትግል ነው እንዳንል፤ የነበረው ዘረፋ ጉዳዩ ትግል ብቻ እነዳልነበረ ያሳብቃል፡፡ የዘረፋው ሰለባ ከሆኑት ሰዎች እንዱ ሲነግረኝ፤ አንዳንድ ሰዎች ሽብሩ እንደተጀመረ፤ ከዘረፋው ለመቋደስ፤ የማዳበሪያ ቀረጢታቸውን ይዘው ይተሙ ነበር፡፡ ቡቲኮችና የንግድ መደብሮች ተዘርፈው፤ አንድ ዙር በማዳበሪያቸው ይዘው የመጡትን ዝርፊያ ቤታቸው ዘርግፈው፤ እንደገና ልጆቻቸውን ማዳበሪያ አስይዘው አስከትለው ለሁለት፤ ሶሰት ዙር ዝርፊያ የተመላለሱም እንዳሉ ሰምተናል፡፡ በዝረፊያ ብቻ በማሯቸው፡፡ ማቃጠል፤ ማንደድ፤ ማውደም፤ መግደል ምን ይባላል፤ ይሄ ኢትዮጵያዊም፤ ኦሮሟዊም ምግባር አይደለም? የኦሮሚያን መስተዳድር ክሽፈት የሚያሳይ ድርጊት እንጂ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ፤ ወንድወሰን እንዳለው ከ29 አመታት በኋላም፤ ለአቅመ አዳም/ሄዋን ያልደረሱ፤ ከፕሮፌሰር መሰፍን ቃል ስዋስ ደግሞ፤ “የከሸፉ” ክልሎች አሉ፡፡ ኦሮሚያ አንዱና ዋንኛው ነው፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስ እለት፤ በቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር፤ ይህ ህዝብ ምን አደረገ፤
1 የምስኪኖች ሰቆቃ እና የነገሌ ግፍ || ልጅ ወንድወሰን ተሾመ (ኢጆሌ ነገሌ-ከዲሲ) July 3, 2020, https://ethiopianege.com/archives/13640ለረጅም ግዜ፤ የነገሌ ከተማ ብቸኛ ታቦት፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነበር፡፡ ባለፉት 20 አመታት ግን፤ ሌሎች ተጨማሪ አብያተ ክርስቲያናት ተተክለዋል፡፡ ቅዱ ጊዮርጊስ ግን፤ የጥንቱ ነው፡፡ የጠዋቱ፡፡ ማክሰኞ፤ ሰኔ 23፤ የቅዱስ ጊዮርጊ እለት፤ በመዘረፍ ብቻ መዳን ምኞት ነው፡፡ ቅንጦት፡፡ መሞትም አለና፡፡ የሚዘርፉት ደግሞ፤ ሰነፎችና ዱላ ይዘው መዞር የሚወዱ፤ ሰው በሰራውና በላቡ በገነባው ህንጻ አይናቸው ደም የሚለብስ፤ በከተማው መስተዳደር የሚታገዙ ቀናተኞችና ምቀኞች ናቸው፡፡ ምናልባት፤ በደም እንጂ፤ በባህርይ ኦሮሞዎች አይደሉም፡፡ ከመስተዳድሩ አባላት የወጣ ሊሆን የሚችል ስም ዝርዝር ተይዞ፤ የእከሌ ቤት ይዘረፍ፤ የነእከሌን ቤት ተዉት እየተባለ እንደሆነ የሚያሳዩ የሰዎች ምስክሮች/ማስረጃዎች አሉን፡፡ ሽብርተኞቹ ሽብራቸውን ተረጋግተውና ሰኣታት ወስደው ነው ያካሄዱት፡፡ አንዳንዶች ባሀብቶች፤ የአያት የቅድመአያቶቻቸውን ስም እየጠሩ፤ በዘራቸውና በገንዘብ ተደራድረውና ተከራክረው ንብረታቸውንም ሕይወታቸውንም ከአሸባሪዎቹ አድነዋል፡፡ አንዳንድ የሸዋ ኦሮሞዎች ንብረትም ተቃጥሏል፡፡ ተጠቂው ሁሉም ነው፡፡ አማራው፤ ጉራጌው፤ ስልጤው፤ ጎንደሬው፤ ሸዌው፤ ደቡቡ፡፡
ይሄ ህዝብ ምን አደረገ? የእኩል እርሻ አረሰ፤ ንግድ አስፋፋ፤ ስራ ፈጠረ፤ ጸጥ ብሎ አደረ፤ ተገዛ፤ መብቱን ሲነጠቅ፤ አሜን ብሎ ተቀበለ፤ በኖረበት፤ በተወለደበት፤ ባደገበት፤ ግብር በሚከፍልበት ቀዬ እንደሁለተኛ ዜጋ ሲታይ ይሁን ብሎ አደረ፡፡ ሁሉም ነገር ተወሰዶበት በኖረ፤ እንደገና ወሮና ከቦ ሕይወትን መንጠቅ ምን ይባላል? ሕዝቡ ቻይ ስለሆነ፤ ከድንቁራና ጋር አልዳረቅም፤ ችግሩን ጊዜ ይፈታዋል ብሎ እንጂ እኮ፤ እስካሁን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሚደረገው ሁሉ ሕገመንግስታዊ አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሕገመንግስት፤ አንዱን ብሄር ባንደኛው ላይ አያነግስም፡፡ ይሄ ሀይ ባይ ያጡ፤ ያልተወከሉ የብሄር ወኪሎች ለብሄራቸው የጫኑት ኢ-ሕገመንግስታዊ ስልጣን እንጂ፤ ሕገመንግስቱ፤ ኦሮሞዎችን የኦሮሚያ አንደኛ፤ ሌሎችን ሁለተኛ አያደርግም፡፡ ይሄ ሁሉ ሲሆን፤ የፌደራል መንግስት የትነበር? ዘግይቶ ደርሷል፡፡ አብይ አሕመድ፤ በሁሉም አቅጣጫ፤ የቀረውን እንጥፍጣፊ ተቀባይነት እያጣ ነው፡፡ ሁሉንም አስደስታለሁ ሲል፤ ሁሉንም አያጣ ነው፡፡
የአብይ ቸልተኝነት፤ ዋጋ እያስከፈለን ነው፤
ይሄ ደም መፋሰስ እንደሚከሰት፤ አብይ ሁለት ሶስት ፍንጮች ነበሩት፡፡ የማንቂያ ክስተቶች፡፡ ላለፉት ሁለት አመታት ሰዎች ሲገደሉ፤ አብያተ ክርስቲያናትና መስጆዶች ሲቃጠሉ፤ ዝም አለ ወይም የማያዳግም እርምጃ አልወሰደም፡፡ እንደውም ባለፈው ጥቅምት፤ ከ86 በላይ ሰዎች ሲደገሉ፤ አብይ ከቀናት በኋላ ነው ሚዲያ ላይ ወጥቶ የተናገረው፡፡ ለዚያውም በዚያ ጉዳይ ላይ፤ እርሙን ሊናገር ቢወጣ፤ የሟቾችን ቁጥር በብሄር ከፋፍሎ መጣ፡፡ 50 ኦሮሞ፤ 30 አማራ፤ 10 ጉራጌ እያለ ይቀጥላል፡፡ ሬሳ ብሄር የለውም፡፡ በዚያን ግዜው ጥቃት፤ በዶዶላ፤ ከ10 ሰዎች በላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፡፡ እንዲያውም ቤተክርስቲያን ውስጥ ሁሉ ጥቃቱ እንደተፈጸመ ማስረጃ አለ፡፡፡ ለዚያውም ቢሆን፤ ድርጊቱን የፈጸሙ ሰዎች ለፍርድ አልቀረቡም፡፡ ዝም ተባለ፡፡ እንዚያ በእቁላለሉ ግዜ ያልተቀጡ ሰዎች ናቸው፤ አሁን ግመል መስረቅ ውስጥ የገቡት፡፡
አብይ ስልጣን ሲይዝ፤ መንግስት ወደድሮው የሀይል አገዛዝ ዘዴ ላለመለስ ቃል ኪዳን ነበረውና፤ በተወሰነ መልኩ የወቅቱን የአብይ ትእግስት መረዳት ይቻላል፡፡ ግን ተደጋገመ፡፡ በዛ፡፡ ሴቶች፤ አራሶች፤ ቄሶች፤ አረጋዊያን፤ ቤተሰቦች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው፤ አስከሬናቸው በምድር ተጎተተ፤ ተቃጠለ፤ ተሰቀለ፤ ከሰለ፡፡ ያ በቂ ምልክት ነበር፡፡ የአካባቢ ሁቱዎች ሲፋፉ እየተመለከተ፤ መንግስት እንዝህላልነቱን ቀጠለ፡፡ በመንግስት እንዝህላልነት ምክንያት፤ ምስኪን ቱትሲዎች ዋጋ ከፈሉ፡፡ በዚህ ረገድ፤ የፌደራሉም፤ የክልሉም መንግስት ከድተውናል፡፡ ሀላፊነታቸውን አልተወጡም፡፡
ልክ ሰኞ ማት፤ ሰኔ 22፤ ሀጫሉ ተገደለ ሲባል፤ በማግስቱ ሊመጣ ያለውን መኣት፤ እንኳንስ የሙሉ ግዜ ስራው ሰላምና ጸጥታ ማስከበር የሆነው መንግስት፤ ማንም ተራ ሰው መገመት ይችላል፡፡ ሞቱ በተነገረ በሰኣታት ግዜ ውስጥ፤ መንግስት፤ ከሚኒሶታ ጀምሮ ከኢትዮጵያ ተከትሎ የሚተላለፈውን የዘር ማጥፋት ጥሪ ዝም ብሎ ኮሞኮመ፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲተላለፍ ካየሁት ቪዲዮ እንደተረዳሁት፤ በነገሌው ኬዝ፤ አንዲት ሴት፤ የነገሌን መንገድ መግቢያና መውጫ ብትዘጉት፤ መንዜ መሄጃ የለውም ስትል ተሰተምታለች፡፡ አንዳንዶች ሀጫሉን የገደለው ነፍጠኛው ነው ሲሉ ሁሉ ተደምጠዋል፡፡ የተማሩትም ጭምር፡፡
መንግስት ሰራዊቱንና ፖሊስ በተጠንቀቅ ማቆምና ስጋት ባለባቸው ቦታዎች ማሰማራት ሲገባው፤ ያን ባለማድረጉ ምክንያት፤ ምስኪን ኢትዮጵያዊያን በብዙ የኦሮሚያ ከተሞች ታረዱ፡፡ ንብረት ወደመ፡፡ መንግስት ባለበት አገር፡፡ ይህ የሆነው፤ መንግስት የአመጥ እንቅስቃሴ ወይም የትጥቅ ትግል አለባቸው ባለባቸው አካባቢዎች ብቻ ቢሆን ኖሮ አይገርመኝም ነበር፡፡ ሰላማዊ በመሰሉ ከተሞች፤ ሻሸመኔና ነገሌ፤ ዝዋይ፤ አሳሳ፤ ደም ፈሰሰ፡፡ በመሀል አገር ይህ ከሆነ፤ በዳር አገር የሚሆነውንማ አስቡት፡፡
መንግስት ለምኔ፤ እና ሕግመንግስቱ፤
መንግስት የተቋቋመው፤ እንደአውሬ ከመሆን እንዲታደገን ነው፡፡ ከሰየጠነ የተፈጥሮ አገዛዝ ወደሰለጠነ የስምምነት አስተዳደር እንዲመልሰን ነው፡፡ መንግስት ያስፈለገው፤ ወደ State of Nature (ወደአውሬነት) ከመመለስ እንዲቤዠን ነው፡፡ ያንን ካላደረገ፤ የመንግስት የመኖሩ አስፈላጊነት ያበቃል፡፡ ሕዝብን ስራው እንዲያወጣው መተው ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አንዱ ላንዱ አያንስም፡፡
ነገሌ እንደዚያ ነው የሆነው፡፡ ቁስቋምና አንዳንድ ሰፈሮች እስከምሽቱ 11 ሰዓት ድረስ በዱላ ብቻ ተፋልመው ራሳቸውንናቤተሰባቸውን ጠብቀዋል፡፡ ብዙዎቹ ሽብርተኞች በክላሽ ጩከት አይደለም፤ በቆመጥ ብቻ የሚበተኑ ፈሪዎች ናቸው፡፡ ሕዝቡ ያልተደራጀው፤ ፖሊስና ልዩ ሀይልን፤ ብልጽግናን ፍራቻ ነው፡፡ ሕዝቡ ሲደራጅና ሲጠነክር፤ ልዩ ሀይል/ፖሊስ ከነፍሰገዳዮቹ ጎን ይሰለፋል፡፡ እንጂ፤ ሕዝቡ ራሱን እንዲከላከል ቢተው፤ በደንብ ይመክታል፡፡ የአካባቢው ባለስልጣናት ግን፤ ሕዝብን ያጠቃሉ፡፡ ያስጠቃሉ፡፡ ለምሳሌ፤ በግድያው ማታና በማግስቱም፤ አላገግባብ የታሰሩ ሰዎች እንዳሉ፡፡ ስላልሞቱ፡፡ ስለተረፉ፡፡ ሰውን ለምን ተረፍክ ብሎ ማሰር የጤና ነው? ከግድያው ቀደም ባሉት ቀናት፤ የአንዳንድ አማራዎች ቤቶች መሳሪያ ደብቃችኋል በሚል ሰበብ ይፈተሸ እንደነበርም ሰምተናል፡፡ ከዚህ በፊት ራሳቸውን ለመከላከል፤ ሊያጠቃቸው በከበባቸው ቡድን ላይ መሳሪያ ወደሰማይ የተኮሱ ሰዎች እንደታሰሩም ምስክሮች ተናግረዋል፡፡ ለዚህ ነው በዚህ ጥቃት ውስጥ፤ የከተማው መስተዳደር፤ የአካባቢው መንግስት ባለስልጣናት እጅ አለበት የምንለው፡፡
ችግሩ ግን ከሕገመንግስቱ አፈጻጸም/አተረጓጎም/አረዳድም ጭምር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕገ-መንገስት ዘረኝነትን ስለሚያስፋፋና ስለሚያፋፋ፤ ቶሎ ይሻሻል ወይም ይቀየር ወይም ይጣል ከሚሉት ውስጥ አይደለሁም፡፡ ብዙ ችግሮች ቢኖሩበትም፤ ይህ ሕገመንግስት በመርህ ደረጃ፤ የዜጎችን የእኩልነት መብት ያረጋግጣል፡፡ አንቀጽ 25 ማናቸውም ኢትዮጵያዊ በዘሩ፤ በእምነቱ፤ በጾታው በሌሎችም
ምክንያቶች ልዩነት/መድልዎ አይደረግበትም ይላል፡፡ አንቀጽ 10፤ የዜጎችና የህዝቦች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይከበራል ይላል፡፡ አንቀጽ 13፤ የፌደራሉም የክልልም መንግስታት በምእራፍ 3 የተዘረዘሩትን መሰረታዊ መብቶች ማክበር ማስከበር አለባቸው ይላል፡፡ ሕገ መንግስቱ ሰብአዊ መብትን ለመጠበቅ በቂ አንቀጾች አሉት፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የጠፋው ሕገመንግስታዊነት ነው፡፡ የምንገዛው፤ ሕገመንግስታዊነት ባልገባቸው የእውቀት ጨዋዎች ነው፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ፤ የግለሰቦች መብት ወደክልል ሲወርድ ይሸራረፋል፡፡ የክልሎችን ስልጣንና ባለቤትነት በተመለከተ፤ ክልሎች አብላጫ የብሄሮች ቋንቋ በሚናገሩት ሰዎች ቢሰይምም፤ የዚያ ክልል ባለቤት ያ ብሄር ብቻ ነው ማለት አይደለም፡፡ የፌደራሉ ሕገመንግስት ውስጥ ክልሎችን ለብሄሮች በባለቤትነት የሚሰጥ አንቀጽ የለም፡፡ ኦሮሚያ በኦሮሚያ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ እንጂ የኦሮሞዎች ብቻ አይደለችም፡፡ ኦሮሞና ኦሮሚያ አንድ አይደሉም፡፡ ኦሮሚያ፤ በክልሉ ውስጥ የሚኖሩ፤ ወደፊትም መጥተው መኖር የሚፈልጉ ሁሉ ነች፡፡ ሌላም ቦታ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መጥተው መኖር፤ የክልሉ ባለቤት መሆን ይችላሉ፡፡
የኦሮሚያ ሕገመንግስት የክልሉን ባለቤትነት ስልጣን ለአንድ ብሄር ሰጠ ማለት፤ ያ ትክክል ነው ማለት አይደለም፡፡ በዚህ ረገድ፤ የኦሮሚያ ሕገመንግስት የፌደራል ሕገ-መንገስቱን ይጥሳል፡፡ ማናቸውም ሕጎች፤ ልማዶች፤ አሰራሮች ከፌደራል ሕገመንግስቱ ጋር መጋጨት የለባቸውም፡፡ ሕገ-መንግስቱን ሳይሆን፤ ይሄንን የተንሻፈፈና የተዛባ፤ ሌሎች ኢትዮጵያዊያንን የባለቤትነት ስልጣን የሚያሳጣ ትርጉም፤ ልማድና አሰራር ነው ባስቸኳይ ማስወገድ ያለብን፡፡
የክልል ሕገ-መንግስት፤ የክልል ክሽፈት፤
የኦሮሚያ ሕገ-መንግስት፤ እኛ ኦሮሞዎች ብሎ ይጀምርና፤ አንቀጽ 8፤ የክልሉን ሉአላዊነትና የመንግስት የስልጣን ባለቤትነት፤ ለኦሮሞ ሕዝብ ብቻ ይሰጣል፡፡ በኦሮሚያ ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች አናሳ ብሄሮች የባለቤትነት ቦታ የላቸውም፡፡ ሰፋሪዎች እንጂ፡፡ አንቀጽ 14(6)፤ ኦሮሞነትን ሲተረጉም፤ የኦሮሞ ቋንቋ የማይናገረውን፤ ከትርጉሙ ውጪ ያደርገዋል፡፡ አናሳ ህዝቦች ወይንም ኦሮሞ ያልሆኑ ሰዎች፤ በኦሮሚያ ሕገመንግስታዊ ጥበቃ የላቸውም፡፡ የራስን እድል በራሳቸው የመወሰን መብት የላቸውም፡፡ የኢትዮጵያ ሕገመንግስት አንቀጽ 13(1)፤ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት፤ በምእራፍ 3 የተቀመጡትን ድንጋጌዎች፤ መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶች የማክበር/የማስከበር ግዴታ ቢጥልባቸውም፤ የኦሮሚያ መንግስት፤ እነዚህን መብቶች ማክበርም ማስከበርም አልቻለም፡፡ ባለቤትነት ይቅር፤ የኦሮሚያም የፌደራሉም ሕገመንግስት፤ ሌሎች ዜጎች፤ በኦሮሚያ ውስጥ፤ ሀብት የማፍራትና የመኖር መብት አላቸው ቢልም፤ ያለፈው የሰኔ 23ቱ ድርጊት የሚያሳየው፤ ያ መብት ባዶ እንደሆነ ነው፡፡
ይህ የሰኔ 23ቱ አይነት ክስተት ሲከሰት፤ ማለትም የክልል መንግስታት፤ የዜጎች መሰረታዊ መብትና ነፃነትን የሚፃረር ተግባር ከፈፀሙ፤ የእርምት እርምጃ እንዲወስዱ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት መመሪያ ይሰጣል፡፡ ይህንንም አክበረው ካልተገበሩ የፌደራል መንግስት የፀጥታ ሃይል ጣልቃ የመግባት ህገ መንግስታዊ ገዴታ ተጥሎበታል። በአጠቃላይ፤ የኦሮሚያ መንግስት እንደመንግስት፤ ከሽፏል፡፡ እንደ ህዝብስ? በክልሉ ውስጥ አብዛኛኛው ኦሮሞ የሆነ ማህበረሰብ (የጋራ ታሪክ፣ ማህበራዊ ኑሮ፣ ልማድ እና ሌሎች የሚየስተሳስሩ ነገሮች እንዳሉ ሆነው) እንዴት ይህ ሰብአዊ ግፍ ተደጋግሞ ሲከስት ማስቆም/መግታት ተሳነው? ይህ እጅግ በጣም አሳሳቢና በሚገባ ልንወያይበት የሚገባ ጉዳይ ነው። መንግስት ከሸፈ፡፡ እንደ ህዝብ፤ ኦሮሞ እንዳይከሽፍ መጠንቀቅ አለበት፡፡የባለፈው ማክሰኞ ክስተት ሲደጋገም ስትመለከቱ፤ የኦሮሚያ መክሸፍ እንደደረሰ እወቁ፡፡
ሕገ-መንግስቱ ያሰራል፤ ግን ይሰራበት፤ የተንሻፈፈው ትርጉሙ ይቃና
http://www.ethcriminalawnetwork.com/system/files/Lak_1_Bara_1987%5B1%5D.pdf ይሄንን ሕገመንግስት ቀዶ ለመጣል ያሰፈሰፉ ብዙ ሀይሎች አሉ፡፡ እሱ አያዋጣም፡፡ አሁንም ለዚህ ህገመንገስት የሚሞቱ አሉ፡፡ ይሄ ሕመንግስት ለብዙዎች አሁንም ድረስ ትኩስ ነው፡፡ ሕያው ነው፡፡ ከምንምነት ክልል፤ ከዞንንት ክልል የሆኑበትና ለመሆን የሚሰናዱበት፤ አገር ለመሆንም የቋመጡበት አሉ፡፡ ይሄንን ሕገመንግስት መቀልበስ ከባድ ነው፡፡ 25 አመት አዝልቆናል፡፡ ባንዴ ለመናድ መሞከር አገሪቱን መናድ ሊሆን ይችላል፡፡ ኢህአዴግን አፍርሶ ብልጽግናን መመስረት፤ አብይንና ለማን እንደለያያቸው፤ የኦሮሞና የትግራይ ብሄርተኞችን እንኳን በአብይ ላይ እንዴት እንደቀሰቀሳቸው እያየን ነው፡፡ ትናንት አይንና ናጫ፤ ገራፊና ተገራፊ የነበሩ ሀይሎች ሁሉ አብረው ሲቆሙ እያየን ነው፡፡ የብልጽግና ምስረታ፤ ፍጥጫውን አብሶታል፡፡ ወደአሃዳዊነት የመመለስ ፍራቻ የቀድሞ ባላንጣዎችን ሁሉ በአንድነት ያቆማል፡፡ ስለዚህ ለጊዜው መታገል ያለብን፤ ሕገመንግስቱን ለመቀየር ሳይሆን፤ ሕገመንግስታዊነትን ለማስፈን ነው፡፡ ሕገመንገስታዊነት ከሰፈነ፤ ይሄ ሕመንግስት፤ ሌላ ክፍለዘመን ሊያኖረን ይችላል፡፡
ከሕገመንግስቱ ጋር ቀጥታ መላተም አያስፈልግም፡፡ በዚሁ ሕገመንግስት የዜግነት መብታችን ይከበርልን፡፡ ኦሮሚያ፤ የኦሮሞ ብቻ ተደርጋ የተሳለችበትና የተተረጎመችበት አግባብ ይቃና፡፡ ያ የትርጉም ስህተት ነው፡፡ ኦሮሚያ፤ በጣም ከጠበበ በውስጧ የሚኖሩ ሁሉ፤ ከለጠጥነው የሁላችንም ናት፡፡ ሁላችንም እናስፈልጋለን፡፡ ሁላችንም የመንግስት ጥበቃም ያስፈልገናል፡፡ የኦሮሚያ መንግስት፤ ጠንካራ የሕዳጣን/አናሳዎች መብት ጥበቃ መዋቅር ካላበጀ፤ የከሸፈ ክልል መሆኑን ይቀጥላል፡፡ ምናልባት ይሄ አማራውና ጉራጌው፤ ስለጤውና ሀድያው ላይ ብቻ የሚያቆም ከመሰለን፤ ተሳስተናል፡፡ በአርሲዎች ዘንድ፤ ጉጂዎችም አናሳ ናቸው፡፡ በጉጂዎች ዘንድ፤ ሜጫና ቱለማም አናሳ ነው፡፡ የጭቆና ሰንሰለት፤ ጫፍ የለውም፡፡
አሻጋሪው አብይና፤ አስገድዶ ደፋሪው ባል
አብይ ይሄን ስልጣን የያዘው ወዶ ነው፡፡ በግድ አሻግራችኋለሁ፤ እንደውም እግዚአብሄር ኢትዮጵያን አድን ዘንድ የቀባኝ ነኝ ሁሉ
ብሎ የሚያምን ይመስለኛል፡፡ እኛም እንደመጣ ንግግሩንና ስብከቱን፤ የወሰዳቸውንም አንዳንድ አዎንታዊ እርምጃዎች አይተን ይሄ ሰው በርግጥም በእግዚአብሄር የተቀባ ይሆን እንዴ ብለን ነበር፡፡ ትእግስቱ መብዛቱን፤ አንዴ ስንወቅስ፤ አንዴ ስናወድስ፤ ሌላ ግዜ ስንከልስ እዚህ ደረስን፡፡ አብይ በውዴታ ሀላፊነት ከወሰደ፤ ያንን ሀላፊነት በብቃት መወጣት አለበት፡፡ ሀላፊነትን ላለመወጣት ምንም ሰበብ የለም፡፡ ስራ እንጂ፡፡ የሚገደለው እኮ፤ ሰው ነው፡፡ ዝንብ አይደለም፡፡ ዛሬ የምስኪኖችን አስከሬን የጎተቱ ሰዎች፤ ነገ የሱን አስከሬን እንደማይጎትቱ ዋስትና የለም፡፡ ካንቀላፋ፤ ይቀድሙታል፡፡ ማንቀላፋቱ፤ እንደፖለቲካዊ ስትራቴጂም፤ እንደሕገመንግስታዊ ጉዳይም አያስኬድም፡፡
አብይ፤ በቀጥታም ይሁን 28 አመት ተሰጥቶት ይህቺን አገር መለወጥ ያልቻለ ፓርቲ ራስ ነው፡፡ ያ ፓርቲ፤ ስም ለውጦ ብልጽግና መጣ፡፡ እኛ የስም ለውጥ አይደለም የምንፈልገው፡፡ የባሕርይ እንጂ፡፡ ኢህአዴግም እንበለው ብልጽግና፤ 29 አመት ይህቺን አገር አስገድደው ደፈሩ፡፡ ይሄንን የፌደራል ስርአት ወለዱ፡፡ መቼስ በአስገድዶ መደፈር ቢወለድም፤ ልጅ፤ ልጅ ነው፤ አገር ነው ብለን ተቀብለን ኖርን፡፡ ልጅ ልጅ ነው፤ ዱርዬም ይሁን ጨዋ፤ ወንጀለኛም ይሁን ሰላማዊ፤ ዲቃላም ይወለድ በትዳር፤ ልጅ ልጅ ነው፡፡ ግን ልጅ ማደግ አለበት፡፡ የተፈጥሮ ጉድለት፤ በሽታ፤ እንከን ከሌለበት በስተቀር፤ ልጅ 18 አመት ከሞላው ልጅ አይደለም፡፡ አዋቂ ነው፡፡
ሙሉ ሰው፡፡ ክልሎች፤ በዚህ ሕገመንገስት ከተወለድን 25 አመት ሞላን እኮ፡፡ ከሽግግር መንግሰቱ ጋር 29፡፡ ይሄ ስርአት እኮ ለ30 አንድ ፈሪ ነው፡፡ እንደግ እንጂ፡፡ ምንድነው አድሮ ጥጃ፡፡ ይሄንን ስርአት በኢትዮጵያ ላይ ለማሳደግና ለአቅመ አዳም/ሄዋን ለማድረስ 30 አመት ካልበቃ፤ ችግር አለ፡፡
የክሽፈት ትርክት፤
የሀጫሉን ሞት ተከትሎ በኦሮሚያ በኢትዮጵያዊያን ላይ የተፈጸመው ግፍ፤ የኦሮሙማ ተቃራኒ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የአማራም፤ የኦሮሞም፤ የትግሬም፤ የወላይታም፤ የሌሎችም ጀግኖች ነበሯት፡፡ ሴትና ሕጻናት፤ ሽማግሌዎችና ካህናት፤ ያልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎችን መግደል ግን፤ ጀግንነት አይደለም፡፡ ትግልም አይደለም፡፡ ለአቅመ አዳም አለመድረስና አገር ወይም ክልል ማስተዳደር አለመቻል ነው፡፡ በውስጣቸው የሚኖሩትን ዜጎች ሕይወትና ንብረት መጠበቅ ካልቻሉ፤ ክልሎች ለአቅመ ክልልነት አልደረሱም፡፡ የአብይና ሽመልስ መንግስት፤ የዚህን ጥፋት ምንጭ ከስር ከመሰረቱ ካልመረመሩና እርምጃ ካልወሰዱ፤ የክልሉ መክሸፍ እውነት ይሆናል፡፡
Do you know that, the Oromos didn’t accept the OPDOs leadership. There is government, they are criminal gangs who have been killing andnlooting for the last 28 b years, with their x masters. OPDO, with its leader is eligimate.
If people elect their own leaders, this wouldn’t have happened. The longer this criminals continue to languish on power, the worse the over all condition will be.
The more, the old and the backward system mongers join the criminal group on power, the worse the condition will be.
Solution:
Free the people let the people get back the power, let the Abba Gadaas rule, the peace would get restored in days.
“ኦሮሚያ በኦሮሚያ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ እንጂ የኦሮሞዎች ብቻ አይደለችም፡፡ ኦሮሞና ኦሮሚያ አንድ አይደሉም፡፡ ኦሮሚያ፤ በክልሉ ውስጥ የሚኖሩ፤ ወደፊትም መጥተው መኖር የሚፈልጉ ሁሉ ነች፡፡ ሌላም ቦታ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መጥተው መኖር፤ የክልሉ ባለቤት መሆን ይችላሉ፡፡” ሲያምርህ ይቅር! ልጋጋም ነፍጠኛ!