በአቪዬሽን ጥራት ማረጋገጫ መስፈርት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአፍሪካ 1ኛ ፣ ከዓለም 20ኛ...

በአቪዬሽን ጥራት ማረጋገጫ መስፈርት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአፍሪካ 1ኛ ፣ ከዓለም 20ኛ ደረጃ አገኘ

ADDIS ABABA, ETHIOPIA - APRIL 4 : Ethiopian Transport Minister Dagmawit Moges speaks during a press conference on "Boeing 737 Max 8" crash in Addis Ababa, Ethiopia on April 4, 2019. (Photo by Minasse Wondimu Hailu/Anadolu Agency/Getty Images)

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዘርፍን ጫና ቢያሳድርበትም፤ ተወዳዳሪነቱና ተፈላጊነቱን ማስቀጠል እንደተቻለ ተነገረ።

ይህንን ያሉት የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ፤ በመናኽሪያዎችና በትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ አካባቢዎች ላይ የኮቪድ-19  ቫይረስ መከላከያ ተግባራት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።
 ዘርፉ የኮሮና ወረርሽኝ ጫናና ተጋላጭነት ቢያሳድርበትም፣ጨተወዳዳሪነቱና ተፈላጊነቱን ግን መጨመሩን ያመላከቱት ሚኒስትሯ፤ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመቀናጀት ወረርሽኙ በዘርፉ  የሚያሳድረውን ተጽዕኖ በመቀነስ ውጤት እንደተገኘበትም አብራርተዋል።
አየር መንገዱ ከ100 ሺኅ  በረራዎች የአውሮፕላን አደጋ ተቀባይነት ያለው 0 ነጥብ 4 ነጥብ በማምጣት መቶ በመቶ አፈጻጸም ማስመዝገቡን የተናገሩት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፤ ዓለም ዐቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መስፈርትም በኦዲት ሥራ 91 ነጥብ 7 በመቶ በማስመዝገብ ከአፍሪካ አንደኛ፣ ከዓለም 20ኛ ደረጃን ማግኘቱን ይፋ አድርገዋል።
በዘርፉ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የተቀመጡትን የሥራ አመራር ሥርዓት የጥራት መስፈርት በማሟላት ዓለም ዐቀፍ የጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት (ISO 90001.2015) እንዳገኘ መረዳት ተችሏል።
በመናኽሪያዎችና በትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ወረርሽኙን ለመከላከል እየተከናወኑ ያሉት ተግባራት እንደሚጠናከሩም ሚኒስትሯ አረጋግጠዋል።

LEAVE A REPLY