የአ/አ ፖሊስ በከተማዋ በሚገኙ ሆቴልና ፔንሲዮኖች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ እያደረገ ነው

የአ/አ ፖሊስ በከተማዋ በሚገኙ ሆቴልና ፔንሲዮኖች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ እያደረገ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ የከተማዋን ደህንነትና ጸጥታ ለመጠበቅ በህጋዊ መንገድ ማህበረሰቡን የማደራጀትና የመኝታ አገልግሎት የሚሰጡ ሆቴል፣ ፔንሲዮንና መሰል ቤቶች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ እያደረግሁ ነው አለ።

ማህበረሰቡ በከተማው ጸጥታና ደህንነት እንዲረጋገጥ በዓመት ለማህበረሰብ ዐቀፍ ተቀጣሪ ጠባቂዎች ከ25 ሚሊዬን ብር በላይ እንደሚከፍል ያስታወሱት በኮሚሽኑ የማህበረሰብ ዐቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ኃላፊ ኮማንደር ሰለሞን ፋንታሁን፤  በከተማዋ የሚታየውን ድንገተኛ ችግሮች ለመፍታት ፖሊስ ብቻውን የሚያደርገው እንቅስቃሴ አጥጋቢ ባለመሆኑ የማህበረሰብ ዐቀፍ የፖሊስ አገልግሎት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
ድንገተኛ ችግሮች መጨመራቸውና  ውስብስብ እየሆኑ ከመምጣታቸው ጋር ተያይዞ ማህበረሰቡን ያሳተፈ ሥራ ለማከናወን በየአካባቢው ራሳቸውንና አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ ለማድረግ በዐሥሩም ክፍለ ከተሞች እውቅና ያለው ማህበረሰብን የማደራጀት ሥራ መጀመሩ ተሰምቷል።
ሆቴሎች ቀደም ሲል በየቀኑ የሚያድሩ ሰዎችን ማንነት በአቅራቢያቸው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ሪፖርት እያቀረቡ ቢሆንም፤ አሁን ላይ እየተፈጠሩ ካሉ ችግሮች ስፋትና ክብደት አንጻር ይህንን ማድረጉ ብቻ በቂ አለመሆኑን ኮማንደሩ አስታውቀዋል።
 በከተማዋ የመኝታ አገልግሎት በሚሰጡ ሆቴሎች፣ ፔንሲዮንና መሰል ሥራ ውስጥ በተሰማሩት ላይ ድንገተኛ ፍተሻ እንደሚደረግ ያመላከተው መረጃ፤ በተመሳሳይ በፈቃዳቸው የተደራጁ የአካባቢ ጠባቂዎችም በቅርበት ክትትል እየተደረገ እንደሆነ ያሳያል።
ከከተማው ስፋትና ከወንጀሎች ውስብስብነት አንጻር በቀጠና ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ላይ አንድ ኦፊሰር እንደሚመደብ የተናገሩት ኮማንደር ሰለሞን፤ይሄ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ለማስጨበጥም ሆነ ለሚፈጠረው ችግር ለመድረስ እጅግ ፈታኝ መሆኑን ጠቁመው፤ ስለሆነም በየደረጃው የተለያዩ አደረጃጀቶች ተፈጥሮው እየሠሩ ቢሆንም ወቅታዊ ችግሮች ሲመጡ ከበድ ስለሚል ፈጣንና ወቅታዊ ምላሽ እንዲሰጥ ለማድረግ በዋናነት በሁለት መልኩ እየተሠራ ነው ብለዋል።
ነዋሪው አካባቢውን እንዲጠበቅ ማድረጉ ችግር የሚፈጥረውን አካል ወዲያው አግኝቶ ዕርምጃ እንዲወሰድ ከማድረጉም በላይ የፖለቲካ ዓላማቸውን ለማስፈጸም ሲሉ የተደራጁ አካላት የሚያደርጉ አካላትን እንቅስቃሴ ለማስቆም ይረዳል ተብሎለታል።

LEAVE A REPLY