በአዲስ አበባ በአንድ ሳምንት ብቻ 1 ሺኅ 700 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል...

በአዲስ አበባ በአንድ ሳምንት ብቻ 1 ሺኅ 700 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ ባለፉት ሦስት ሳምንታት ወዲህ በሕብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ መዘነጋት መታየቱን ተከትሎ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በዚህ ወቅት በእጅጉ መስፋፋቱ እየተነገረ ይገኛል።
 ይህንን መዘነጋት ተከትሎ በአዲስ አበባ በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ከ1ሺኅ 700 በላይ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ጉዳዮን አስመልክቶ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ በተለይም ባለፉት ሁለት ሳምንታት እና ሦስት ዓመታት ውስጥ የመዲናዋ ነዋሪዎች የቫይረሱን ሥርጭት ለመቆጣጠር የተቀመጡትን መመሪያዎች ከመተግበር ይልቅ፤ ግልጽ የሆነ መዘነጋት አሳይቷል።
በሕዝብ ዘንድ የታየው መለሳለስና ቸልተኝነት ቫይረሱ በአዲስ አበባ ከተማ በፍጥነት እንዲዛመት አድርጓል ያለው የከተማ መስተዳደሩ መግለጫ ይህንን ተከትሎ ባለፉት ስድስትና ሰባት ቀናት ውስጥ ከአንድ ሺኅ ሠባት መቶ የሚሆኑ ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ እንደሆኑ ጠቁሞ በአንድ ቀን ውስጥ 740 (ሠባት መቶ አርባ ሰዎች) በምርመራ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የሚያሳይ አስደንጋጭ አሀዝ መመዝገቡንም አስታውሷል።

LEAVE A REPLY