የተዘጉት ሁሉም ፍርድ ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ እሰከ ሐምሌ 30 ለሥራ ክፍት እንደሚሆኑ...

የተዘጉት ሁሉም ፍርድ ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ እሰከ ሐምሌ 30 ለሥራ ክፍት እንደሚሆኑ ተደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመቆጣጠር ሲባል በከፊል ዝግ የነበረው የፌደራል ፍርድ ቤቶች የችሎት ሥራ ከዛሬ ጀምሮ ወደ መደበኛ አገልግሎት መስጠት ተመልሷል።

በአዲስ አበባ ፍርድ ቤቶች ከመጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በከፊል ዝግ ሆነው ወሳኝ ጉዳዮች ብቻ በውስን ችሎቶች ሲስተናገዱ መቆየታቸው ይታወሳል።
አሁን ላይ ግን ይህ አሠራር እንዲሻሻል ተደርጓል።  ከዛሬ ሐምሌ 13 ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ በሁሉም ፍርድ ቤቶች የመልስ መልስ፣ አስተያየቶች፣ የትዕዛዝ ውጤቶችን ለመቀበል የተቀጠሩ እና እልባት ለመስጠት ጥቂት ሂደት የቀራቸው ጉዳዮች ፣ እስረኛ ያላቸው መዛግብት በየቀጠሮ ቀናቸው የማስተናገድ ሥራ እንደሚሠራ ይፋ ሆኗል።
የፌደራል ፍርድ ቤቶች ቃል አቀባይ እና የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ተስፋዬ ነዋይ ፤ የሚታዩ ጉዳዮች አስቸኳይነት በዳኛው፣ በፍርድ ቤቱ እንዲሁም በየደረጃው በሚገኝ አመራር አሳማኝነቱ ካልታመነበት ለቀጣዩ ዓመት እንደሚቀጠር፣ በተጨማሪም ፍርድ ቤቶቹ አዳዲስ መዝገቦችን እኔደ የቀጥታ ክስ፣ ይግባኝ እና አፈጻጸም መዝገቦችን ደግሞ ከነሐሴ 1 ቀን እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ማየት እንደሚጀምሩ ይፋ አድርገዋል።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትን በተመለከተ በአዲስ አበባ ከሚገኙ ባለጉዳዮች የሚቀርቡ አቤቱታዎች ይስተናገዳሉ ያሉት ቃል አቀባዮ፤ ከክልል የሚመጡ የሰበር ጉዳዮች ግን የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል ሲባል ተለዋጭ የሥራ አቅጣጫ እስከሚሰጥ ጉዳያቸው እንደማይታይ አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY