ቻይና የአሜሪካ የኮቪድ 19 ክትባት ምርመራ የሚካሄዱባቸው ቤተ ሙከራዎችን ሰለለች

ቻይና የአሜሪካ የኮቪድ 19 ክትባት ምርመራ የሚካሄዱባቸው ቤተ ሙከራዎችን ሰለለች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ቻይና የኮቪድ-19 ክትባት ምርምር የሚያካሂዱ ቤተ ሙከራዎች ላይ ስለላ እያደረገች ነው ስትል አሜሪካ ወነጀለች።

በኮሮና ቫይረስ ላይ የሚደረግ ምርምርን ሰልለዋል የተባሉም ሁለት ቻይናውያን ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን፣ ክሱ የተመሰረተው አሜሪካ ቻይናን በበይነ መረብ ስለላ አምርራ መተቸቷን ተከትሎ መሆኑም ታውቋል።
ባለፈው ሳምንት አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ካናዳ፤ ሩስያ የኮቪድ-19 ምርምር ለመስረቅ ሞክራለች ማለቷ ይታወቃል።
አሜሪካ የከሰሰቻቸው ቻይናውያን የቀድሞ የኤሌክትሪክ ምህንድስና ተማሪዎቹ ሊ ዢያዩ እና ዶንግ ጂአዚ ሲሆኑ፣ ግለሰቦቹ የንግድ ሚስጥር በመስረቅና ለበይነ መረብ የገንዘብ ምዝበራ በመመሳጠር ተወንጅለዋል።
አሜሪካ የከሰሰቻቸው ቻይናውያን የቀድሞ የኤሌክትሪክ ምህንድስና ተማሪዎቹ ሊ ዢያዩ እና ዶንግ ጂአዚ መሆናቸውም ታውቋል።
ዐቃቤ ሕግ እንደሚለው ከሆነ ሁለቱ ቻይናውያን መጋቢት ላይ የማስቹሴትስ የባዮቴክኖሎጂ ተቋምን ሰልለዋል። በዚህ ተቋም ለኮቪድ-19 ክትባት ለማግኘት ጥናት እየተደረገ መሆኑ ተነግሮለታል።
ሜሪላንድ የሚገኘው ድርጅት ኮሮና ቫይረስ ላይ ምርምር እያደረገ መሆኑን አስታውቆ፣ በሳምንቱ ቻይናውያኑ የድርጅቱን በይነ መረብ ሰርስረው ገብተዋል ሲል ክስ መስርቷል።
ተጠርጣሪዎቹ አብዛኛውን ጊዜ በግላቸው በበይነ መረብ መረጃ ቢሰርቁም፤ አልፎ አልፎ የቻይና ሰላዮች ድጋፍ ያደርጉላቸዋል እየተባለ ነው፤ ድጋፍ አድርገዋል ከተባሉት መካከል የቻይና የብሔራዊ ደህንነት ሓላፊ እንደሚገኙበት ታውቋል።
ቻይና የሚኖሩት እነዚህ ግለሰቦች፤ ስለ ኮሮና ቫይረስ ክትባት፣ ሕክምና እና ምርመራ መረጃ ለማግኘት የባዮቴክ ተቋማትን የመረጃ መረብ ደህንነት ለመጣስ ተገደዋል።ከአሜሪካ በተጨማሪ አውስትራሊያ፣ ቤልጂየም፣ ጀርመን፣ ጃፓን፣ ሊቱኒያ፣ ኔዘርላንድስ፣ ስፔን፣ ስዊድን እና ዩናይትድ ኪንግደም ኢላማ መደረጋቸው ታውቋል።

LEAVE A REPLY