ኢትዮጵያውያን ከአንድ ወር በኋላ ፓስፖርት ማውጣትና ማደስ ይችላሉ ተባለ

ኢትዮጵያውያን ከአንድ ወር በኋላ ፓስፖርት ማውጣትና ማደስ ይችላሉ ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከእንግዲህ በኋላ ኢትዮጵያውያን ፓስፖርታቸውን ለማደስ የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በአካል መሄድ አይጠበቅባችሁም ተባለ።

ተቋሙ በአንድ ወር ፣ ከረዘመም በሁለት ወር ውስጥ የፓስፖርት እድሳት አገልግሎትን በኢንተርኔት አማካይነት መስጠት እንደሚጀምር አስታውቋል።
በተግባር ላይ በሚውለው አዲስ አሠራር ፓስፖርታቸውን ማሳደስ የሚፈልጉ ሰዎች በኢንተርኔት ቅፅ ሞልተው በባንክ ክፍያ ከፈጸሙ በኋላ  የታደሰ ፓስፖርታቸውን በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኤጀንሲው ቅርንጫፍ መውሰድ እንደሚችሉ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል ገልጸዋል።
በተመሳሳይ አዲስ ፓስፖርት ማውጣት የሚፈልጉ በኢንተርኔት ለዚሁ ዓላማ የተጋጀውን የኤጀንሲውን ቅፅ ሞልተው በቀጠሯቸው ቀን እንዲስተናገዱ ይደረጋል ያለው
የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ፤ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የፓስፖርት እድሳትም ሆነ አዲስ የመስጠት አገልግሎት በሙሉ አቅሙ እያከናወነ እንዳልሆነ አስታውቋል።
በመሆኑም ችግሩን ለመቅረፍ አገልግሎቱን በሙሉ አቅም ለመስጠት የኢንተርኔት መላ አንደኛው አማራጭ ተደርጎ መወሰዱን አቶ ሙጂብ አብራርተዋል።

LEAVE A REPLY