ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ እቃ ጫኝ አውሮፕላን በቻይና ሻንጋይ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በእሳት መቃጠሉ ተሰማ።
አውሮሮፕላኑ በእሳት የተያያዘው በሻንጋይ አውሮፕላን ማረፊያ እቃ በሚጭነበት ወቅት መሆኑ ተሰምቷል።
ያልታሰበው አደጋ ሁሉም ቢደርስም የአውሮፕላኑ ሠራተኞች በመልካም ደህንነት ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መግለጫ ሰጥቷል።
አየር መንገዱ አደጋውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ቦይንግ 777 ኢቲ ኤአርኤች እቃ ጫኝ አውሮፕላን እቃ ሲጭን በነበረበት ወቅት በእሳት መያያዙን ገልጿል።
አውሮፕላኑ ከሻንጋይ ወደ ሳኦ ፓሎ መደበኛ የካርጎ በረራ ለማድረግ ዝግጅት ላይ የነበረ መሆኑ ነው የተነገረው። በአውሮፕላኑ ላይ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠርም ከሚመለከታቸው ሁሉም አካላት ጋር ኢትዮጵያ በትብብር መስራቷን አየር መንገዱ አስታውቋል።
የእቃ ጫኝ አውሮፕላኑ ላይ የደረሰው የጉዳት መጠንና የእሳት አደጋው መንስዔ በሚመለከታቸው አካላት እየተጣራ እንደሚገኝ ተነግሯል።