በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ 30 ሺኅ ኢትዮጵያውያን ተመለሱ

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ 30 ሺኅ ኢትዮጵያውያን ተመለሱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ||  የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያስከተለውን ተፅዕኖ ተከትሎ በተለያዩ ሀገራት በችግር ውስጥ የነበሩ ከ30 ሺኅ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገር ቤት  መመለሱ ተነገረ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያዩ ሀገራት ለሚገኙ ዜጎች የሚደረገው ድጋፍ እና እርዳታ የቀጠለ መሆኑን ጠቁሞ፤ በሽታው ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ በቤሩት በችግር ላይ የነበሩ 656፣ ከአቡዳቢ 72፣ ከሳዑዲ ዓረቢያ 3 ሺኅ 539፣ ከኩዌት 1 ሺኅ 23 እንዲሁም በድንበር በኩል ደግሞ 24 ሺኅ 797 ዜጎች በጠቅላላው 30 ሺኅ 87 ዜጎች ወደ ሀገር እንደተመለሱም ገልጿል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዮ የመገናኛ ብዙኃን በአስከፊ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የተዘገበላቸው በየመን ያሉ ኢትዮጵያዊያንን በተመለከተ፤ በሀገሪቱ ካለው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ ያለውን የመረጃ እጥረት ለመፍታት እና ዜጎች እርዳታ የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸት ኢትዮጵያ ከሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ የሥራ ሓላፊ ጋር ንግግር እንደተጀመረም ተሰምቷል።
በተያያዘ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን በሚገኙባቸው የተለያዩ የዓረብ ሀገራት መሰል ሥራዎች ከሳዑዲ ዓረቢያ፣ ከኩዌት፣ ከተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች እና ከመሳሰሉት ሀገራት ጋር በትብብር ዜጎችን የመርዳት እና የማገዝ ሥራዎች በመሠራት ላይ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በተለያዩ የዓረብ ሀገራት እና ጎረቤት ሀገራት በችግር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ባሉበት ቦታ መጠለያ፣ ምግብ፣ ሕክምና እና ሌሎች መሠረታዊ ግብዓቶች እንዲሟላላቸው ከማድረግ አንጻር ውጤታማ ሥራዎች ተሠርቶላቸዋል።
የሊባኖስ ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ መጎዳቱን ተከትሎ ከሥራ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያዊያን ወገኖችንን ለማገዝ በቤሩት ከሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንጽላ ጽ/ቤት፣ ከሀገሪቱ መንግሥት፣ ከኢትዮጵያዊን ኮሙዩኒቲ አባላት፣ ከዓለም ዐቀፍ የረድኤት ድርጅቶች  (IOM, ILO) ኢጋድ፣ እንዲሁም ድንበር የለሽ የሐኪሞች ማኅበር ጋር በጋራ በተሠሩ ሥራዎች በችግር ላይ ይገኙ የነበሩ ዜጎች እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሆነም ተገልጿል።

LEAVE A REPLY