ዛሬ 409 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ፣ 9 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል

ዛሬ 409 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ፣ 9 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ በተደረገው 6 ሺኅ 898  የላብራቶሪ ምርመራ 409 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተገለጸ።

በዚህ መሠረት በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 11 ሺኅ 933 እንደ ደረሰ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።
በሌላ በኩል ዛሬ  የ9 ሰዎች ሕይወት በቫይረሱ ምክንያት እንዳለፈና ይህንን ተከትሎ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 197 ደርሷል።
በተያያዘ ዜና ትናንት 139 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 5 ሺኅ 645 መድረሱ ተገልጿል።
ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን 357 ሺኅ 58 ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸው፤ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 11 ሺኅ 993 መሆኑን የጤና ሚኒስቴር በመግለጫው ጠቁሟል።
በዚህ ወቅት ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 6 ሺኅ 89 ደርሷል። ከእነዚህም ውስጥ 65 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውን የገለጸው ሚኒስቴሩ፣እስካሁን በኢትዮጵያ 5 ሺኅ 645 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤  በድምሩ የ197 ሰዎች ሕይወት ማለፉን አስረድቷል።

LEAVE A REPLY