የሶማሌ ክልል ም/ቤት የቀጣይ ዓመት በጀትና አዳዲስ ሹመቶችን ዛሬ አፀደቀ

የሶማሌ ክልል ም/ቤት የቀጣይ ዓመት በጀትና አዳዲስ ሹመቶችን ዛሬ አፀደቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ለውጡን በአግባቡ የተጠቀመበት የሶማሌ ክልል፤ የክልል ምክር ቤት 5ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ አካሂዷል።

በሙስጠፌ መሐመድ የሚመራው የሶማሌ ክልል ምክር ቤት በመደበኛ ጉባዔው የክልሉን የ2013 ዓመት በጀትን ጨምሮ የተለያዩ አዋጆችንና ሹመቶችን ማፅደቁ ታውቋል።
በዚህ መሠረት የክልሉ ምክር ቤት 22 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ሆኖ የቀረበለትን የ2013 የክልሉ መንግሥት በጀትን ተመልክቶ ያፀደቀ ሲሆን፤ ከዓመታዊ በጀቱ 17 ነጥብ 2 ቢሊየን ብሩ ከፌደራል መንግሥት በሚገኝ ድጎማ የሚሸፈን ፣  ቀሪው 5 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ደግሞ በክልሉ የውስጥ ገቢ የሚሸፈን መሆኑ ተነግሯል።
ምክር ቤቱ በጉባዔው የ2012 የክልሉን መንግሥት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በመመልከት አፅድቋል። የክልሉን የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የ2012 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርትና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ ሪፖርቱን ለምክር ቤቱ ማቅረቡ ተሰምቷል።
በተመሳሳይ በጉባዔው የ8 ዳኞች ሹመት ለምክር ቤቱ የቀረበ ሲሆን፤ ምክር ቤቱም የቀረበውን የዳኞች ሹመት በመመልከት በሙሉ ድምጽ እንዳፀደቀው ታውቋል።
 የመንግሥት ሠራተኞች አደረጃጀት ማሻሻያ አዋጅን፣ የገቢ ግብር አስተድስደር አዋጅን እና ለሥራ ምዘና እና ውጤት አሰጣጥ የተጠየቀ ተጨማሪ በጀትን ምክር ቤቱ ተመልክቶ ማጽደቁን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ገልጿል።

LEAVE A REPLY