1 ሚሊዮን ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ኮሮናን መከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

1 ሚሊዮን ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ኮሮናን መከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || “ጤናችን በእጃችን “የሚል መሪ ቃል የተሰጠው የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።

“ሮሃ እና ዳልበርግ” ግሩፕ ከመንግሥት እና ከግብረ ሰናይ ድርጅቶች የጋራ ትብብር ፤ ለቀጣይ ሥድሥት ወራት የሚቆይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል ፕሮጀክት ነው ይፋ የተደረገው።
 በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ የሆኑት ኢንጂነር እንዳወቅ አብቴ እና የሮሃ አፍሪካ ዳይሬክተር ወለላ ኃይለ ሥላሤ በጋራ የድጋፍ ፕሮጀክቱን በጋራ አስጀምረውታል።
“ጤናችን በእጃችን” በሚለው ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከል ፕሮጀክት ተግባራዊ የሚደረገው በቅርቡ ይፋ በሆነው መንደርን መሰረት ያደረገ የብሎክ አደረጃጀት አማካኝነት እንደሆነም ተገልጿል።
 በዚህም 1.2 ሚሊዮን ዜጎችን ቀጥታ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ የሚደረግላቸው ሲሆን፤ በተጨማሪም ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ላይ የባህሪ ለውጥ ለማምጣት ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እንደሚሠሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ  ሴክረታሪያት ቢሮ አስታውቋል።

LEAVE A REPLY