በያዝነው ክረምት ግድቦችን ሊያፈርስ የሚችል ከመደበኛ በላይ ዝናብ ያጋጥማል ተባለ

በያዝነው ክረምት ግድቦችን ሊያፈርስ የሚችል ከመደበኛ በላይ ዝናብ ያጋጥማል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በያዝነው የክረምት ወቅት እና እሰከ መስከረም ባለው ጊዜ ውስጥ ባለው  ዝናብ ምክንያት፤ በተለይም በሰሜን ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ ቦታዎች  ከመደበኛ በላይ ዝናብ ያጋጥማል ተባለ።

 የብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እና በዓለም የሜትሮሎጂ ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ ተጠሪ አቶ ፈጠነ ተሾመ ፤ ዝናቡ ምንም ያህል ቢጨምር በአግባቡ ጥንቃቄ ተወስዶ ከተሠራበት እና በተለይም ግድቦች አካባቢ የጎርፍ አደጋ እንዳይከሰት አስፈላጊው ጥንቃቄ ከተደረገ እንደ መልካም አጋጣሚ መወሰድ ይቻላል ነው ያሉት።
 በበጋው ወራት ደረቅ እና አነስተኛ የውሃ መጠን ሊኖር ሰለሚችል አስፈላጊው የውሃ መከማቸት ሥራዎች እንደሚገባና በግድቦች አካባቢ የሚኖር የውሃ መጠን እና ሙሌት በዝናብ ምክንያት ከፍ ስለሚል የማስተንፈስ ሥራዎች ከመሥራት ባሻገር፤ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ የጎርፍ አደጋ እንዳይከሰት ከመብራት ኃይል ጋር በመሆን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸውም ታውቋል።
 ግድቦች አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች በጎርፍ እንዳይጠቁ ለማድረግ የሚሠሩ መፋሰሻዎችን ለመስኖ ልማት ሲሉ የሚያፈርሱ በመኖራቸው፤ እንደዚህ አይነት ተግባር ከማድረግ መቆጠብ ተገቢ እንደሆነም ዋና ዳይሬክተሩ በመግለጫው ላይ ይፋ አድርገዋል።
ብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ አስቀድሞ ባስቀመጠው ትንበያ መሰረት፤ በሚቀጥሉት ጊዜያት በሚፈጠረው ከባድ ዝናብ ምከንያት በተለይም ግድቦች አካባቢ የሚፈጠርን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛል ያለው ተቋሙ፤ ስጋት ባለባቸው ቦታዎች የጎርፍ አደጋ ቢያጋጥም እንኳን አደጋውን ለመቆጣጠር እንዲቻል የተደራጀ ግብረሃይል ከመኖሩ ባሻገር የጀልባ፣ ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ አቅርቦቶችን ለማቅረብ እንደሚሠራም አስታውቋል።

LEAVE A REPLY