አቪዬሽን 552 ኢትዮጵያውያንና 6 የወጭ ሀገር ዜጋ ባለሙያዎችን አስመረቀ

አቪዬሽን 552 ኢትዮጵያውያንና 6 የወጭ ሀገር ዜጋ ባለሙያዎችን አስመረቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በግዙፉ የኢትየጵያ አየር መንገድ ሥር የሚገኘው የአቪዬሽን አካዳሚ 558 የአቪዬሽን ባለሙያዎች እንዳስመረቀ ተሰማ።

ወቅቱ የኮሮና ቫይረስ የተስፋፋበት መሆኑን ተከትሎ  በቪዲዮ ኮንፈረንስ በተደረገው የምርቃት ሥነ ሥርዓት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያምን ጨምሮ የአቪዬሽን ባለድርሻ አካላት፣ ተጋባዥ እንግዶች እና የተመራቂ ቤተሰቦች መሳተፋቸው ታውቋል።
የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ለተመራቂዎቹ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።  “በዚህች ልዩ ቀን ወረርሽኙ እንድንሰበሰብ ባይፈቅድም በዚህ መልኩ ለማክበር ችለናል” ያሉት ሥራ አስፈጻሚው፤  የተማረ እና የሰለጠነ የሰው ኃይል ለዘላቂ ልማት ዕድገት ወሳኝ እንደሆነም ገልጸዋል።
አየር መንገዱ ዛሬ ካስመረቃቸው መካከል 72 አብራሪዎች፣ 173 የበረራ አስተናጋጆች፣ 7 የአውሮፕላን ቴክኒሻኖች የሚገኙበት ሲሆን፤  የሥድስት ሃገራት ዜጎች በተጨማሪነት በምረቃው ተካትተዋል።

LEAVE A REPLY