ኦ ኤም ኤን ከሰኞ ጀምሮ መንገዶች እንዲዘጉና ከአማሮች ጋር ግብይት እንዳይደረገ...

ኦ ኤም ኤን ከሰኞ ጀምሮ መንገዶች እንዲዘጉና ከአማሮች ጋር ግብይት እንዳይደረገ አድማ ጠራ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኦሮሞ ሕዝብና የአማራ ሕዝብ እርስ በርሱ እንዲጋደል ከፍተኛ የፕሮፐጋንዳ ሥራ እየሠራ የሚገኘው ኦ ኤም ኤን (omn) ቴሌቪዥን ዳግም በኦሮሚያ ውስጥ ግድያና የንብረት መውደም እንዲከሰት በይፋ አድማ ጠራ።

የኹከት ናፋቂው ጃዋር መሐመድ ንብረት የሆነው (ቀጥተኛ ባለመብትነቱ ባይገለጽም የኦነግ ልሳን እንደሆነ የሚነገርለት) ኦ ኤም ኤን ቴሌቪዥን ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በመላ ኦሮሚያ ከፍተኛ የሆነ ብጥብጥ እንዲከሰት ጥሪ ያቀረበው በኦሮምኛ ቋንቋ መሆኑ ፤ መልእክቱ “ውጡ” ሲባሉ ወዴት? “ግደሉ” ሲባሉ ለምን? ብለው ለማይጠይቁ መንጋዎችና ጽንፈኛ ብሔርተኞች እንዲደርስ ታስቦ መሆኑ ታውቋል።
ፍጹም አሳፋሪና ዘር ተኮር የሆነ ጥቃት ዳግም እንዲቀሰቀስ  በይፋ አድማ የጠራው  ኦ ኤም ኤን ቲቪ፤ ከሰኞ ሐምሌ 20-2012  ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከተሞችን የሚያገናኙ መንገዶች እንደሚጉ፣ ማንኛውም ተሽከርካሪ መንቀሳቀስ እንዳይችል ለመንጋ ጥቃት አድራሾች ጥሪ አቅርቧል።
 ይህንን የወረደና ሀገር እንድትጠፋ የሚፈልጉ ኃይሎች ያስተላለፉትን መመሪያ ተላልፎ የተገኘ መኪና እንዲቃጠል ሲልም ቴሌቪዥን ጣቢያው ፈጽሞ የሰላም ጠር ከመሆኑ ባሻገር የሀገርና የግለሰቦች ንብረት እንዲወድም ያለውን ጽኑ ጉጉት ገሀድ አውጥቷል።
በተጨማሪም ” በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚኖሩ ነፍጠኞችን (የአማራ ተወላጆችን) ምንም ዓይነት የንግድ ልውውጥ እንዳታደርጉ፤ ከእነርሱ ላይ አትግዙ፣ ለእነርሱም አትሽጡ!” የሚል የአድማ ጥሪ ያቀረበው ይህ ሚዲያ ዛሬ ቀኑን ሙሉ የአማራ ብሔርን የሚያንቋሽሹና የኦሮሞ ሕዝብ ከአማራ ሕዝብ እንዲጋጭ የሚያነሳሱ ሐሰተኛ ፕሮፐጋንዳዎችን ሲነዛ ውሏል።
ጃዋር፣ ኦ ኤም ኤንና አክራሪ የኦሮሞ ብሔርተኞች ከዚህ ቀደም ያደረሱት ጥፋት በቅጡ የሚታወቅ ከመሆኑ አኳያ መንግሥት መከላከያ ሠራዊትና የፌደራል ፖሊስ አባላትን በክልሉ፣ በተለይም የመንጋ ቡድን አባላትና በፖለቲካ ስም ሃይማኖትና ዘር ተኮር ጥቃት የሚፈጽሙባቸው  አርሲና ባሌ ዞኖች ፣ እንዲሁም ሀረር ክልል በሚገኙ ቦታዎች በማሠማራት ሕብረተሰቡን ከአደጋ እንዲከላከል የተለያዮ አካላት ከወዲሁ ጥሪ እያቀረቡ ነው።

LEAVE A REPLY