ድሮ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሆነው “ሀጊያ ሶፊያ” ቅርስ መስጊድ እንዲሆን ተወሰነ

ድሮ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሆነው “ሀጊያ ሶፊያ” ቅርስ መስጊድ እንዲሆን ተወሰነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከተመሠረተ 1ሺኅ 500 ዓመት ዕድሜ ያስቀምጣሉ ጠረው ዝነኛው ” የሀጊያ ሶፊያ ” ቅርስ መስጊድ እንዲሆን መወሰኑ ይፋ ተደረገ።

በቱርክ የሚገኘውና ቀደም  ባለው ዘመን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የነበረው ሀጊያ ሶፊያ አሁን መስጊድ መሆኑ ተረጋግጧል።  በስነ ግንባታው መላው ዓለም የሚያደንቀው የሀጊያ ሶፊያ ህንጻ በከፊል መስጊድ ሆኖ እንዲያገለግል ውሳኔ የሰጠው ፍርድ ቤት መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል።
በቱርኳ ኢስታንቡል ከተማ  የሚገኘው ሀጊያ ሶፊያ ከዓለም ቅርሶች ልዩ ቦታ የሚሰጠው መሆኑ ይነገርለታል። ውሳኔውን ተከትሎ አስተያየታቸውን የሰጡት የኢስታንቡል ከንቲባ የርሊካያ አሊ፤ “ሙስሊሞች በዜናው ተደስተዋል፤ ጁምዓ ሁሉም ሰው በዚያ ሥፍራ ለመገኘት ይፈልጋል” ብለዋል።
አንድ ሺኅ አምስት መቶ ዓመት ያስቆጠረውና ይህ በዩኔስኮ ልዩ ቦታ የሚሰጠው ታሪካዊ ሕንጻ ወደ ሙዚየምነት የተቀየረው በፈረንጆቹ በ1934 ሲሆን፤ ከዚያ ቀደም ባሉ ረዥም ዓመታት ግን መስጊድ እንደነበር ታውቋል።
 ቅርሱ ወደ መስጊድነት እንዲመለስ መወሰኑ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል፤ ይህም የሆነው ቅርሱ በቢዛንታይን ጊዜ ሲገነባ የዓለም ትልቁ ቤተ ክርስቲያን የነበረ በመሆኑ ነው ተብሏል።
ከዛሬ አርብ ጀምሮ በአንድ ጊዜ አንድ ሺኅ ሰዎች በሀጊያ ሶፊያ ተገኝተው ሊሰግዱበት ይችላሉ ተብሎ የተገመተ ሲሆን፤ ዛሬ ለጁምዓ በመስጊዱ ከሚገኙት ምዕመናን መካከል፣ የቱርኩ መሪ ጣይብ ኤርዶጋን አንዱ እንደሚሆኑ ተጠብቋል።
ኮምጫጫው ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ይህ ቅርስ መስጊድ እንዲሆን መወሰኑን ሲያሳውቁ ብዙዎች ቢደሰቱም በዛው መጠን ከፍተኛ ቅሬታዎችም እየተሰሙ ነው።
የካቶሊኩ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ “ለኢስታንቡል እጸልያለሁ፤ ሳንታ ሶፊያን ባሰብኩ ቁጥር ሐዘኔ ይበረታል” ሲሉ ከውሳኔው በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት የካቶሊኩ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ አንዱ ናቸው፡፡
የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናትም በውሳኔው ሐዘናቸውን ገልጸዋል፡፡ ፓትሪያርክ ባርቶሎሜ ” ይህ ቅርስ መስጊድ መሆኑ የብዙ ኦርቶዶክሶችን ልብ የሚሰብር ነው” ሲሉ ገልጸዋል።
350 ቤተ ክርስትያኖችን ያቀፈው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባዔ በበኩሉ ፤ ውሳኔው እንዲቀለበስ ከመጠየቁ ባሻገር፣ ይህ ውሳኔ አንድነትን ሳይሆን ክፍፍልን የሚፈጥር ነው ሲል አስጠንቅቋል።
ሀጊያ ሶፊያ ከ86 ዓመታት በኋላ ወደ መስጊድነት የተቀየረው የኢስታንቡል ወራሪ የነበረው የሕንጻው ባለቤት በኑዛዜው “ቤቴ መስጊድ ይሁንልኝ” ማለቱን ተከትሎ እንደሆነ ተነግሯል።

LEAVE A REPLY