ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በአፋር ክልል የችግኝ ተከላ አካሄዱ ተብሏል

ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በአፋር ክልል የችግኝ ተከላ አካሄዱ ተብሏል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ||  ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ ዛሬ በአፋር የችግኝ ተከላ ማካሄዳቸው ተሰምቷል።

በችግኝ ተከላው የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አወል አርባን ጨምሮ ሚኒስትሮችና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሓላፊዎች ገለጹ።
በዛሬው ዕለትም ብቻ በክልሉ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ችግኝ እንደሚተከል የተነገረ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አሕመድ የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ዘመቻን ቀደም ሲል በሀዋሳ ማስጀመራቸው አይዘነጋም።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከችግኝ ተከላው ባሻገር በአፋር ክልል በዱብቲ ወረዳ 700 ሄክታር ስፋት ባለው መሬት ላይ የተዘጋጀውን የእንስሳት መኖ ማከማቻ እንደጎበኙ ታውቋል።
ከዐራት ዓመታት በፊት አነስተኛ ስፋት ባለው የመሬት ይዞታ ላይ ይከናወን የነበረው ይህ ሥራ፤ አርሶ አደሮቹ በአሁኑ ወቅት በየ45 ቀናት የሚታጨዱ ልዩ ልዩ የመኖ ሣር ዓይነቶችን በማብቀል ላይ እንዲደርስ አስችሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ ከዚህ ቀደም በረሃማ አካባቢዎች ተብለው ሳይለሙ የቆዩ ቦታዎችን ወደ ሥራ በማስገባት፤ ከውጭ የሚገባ የግብርና ምርት ለመተካት እየተሠራ እንደሆነ ገልጸዋል።
 የመስኖ አካባቢው እስካሁን ሦስት ጊዜ የለማ መሆኑንና በመጀመሪያዎቹ ዐራት ወራት ጥጥ፣ በቀጣዮቹ ሦስት ወራት አኩሪ አተር እና አሁን ላይ በተጨማሪ የእንሰሳት መኖ እየለማበት መሆኑ ታውቋል።
የአፋር ክልል ለጅቡቲ እና ለአሰብ ወደቦች በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ግብርናው የወጪ ንግድ ላይም ትኩረት እንዲያደርግ እንደሚሠራ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ላይ ተናግረዋል።
በሕብረትና በጥረት ከሠራን ራሳችንን በመቻል ከሁለት እና ሦስት ዓመታት በኋላ ስንዴ ከውጭ አናስገባም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤  ዘላቂ ልማትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ ሁሉም ዜጋ ዛፍ እንዲተክል ከመምከራቸው ባሻገር፣
ኢትዮጵያውያን ጨክነን መሥራት ያለበን ዘላቂ ጥቅም እና ለሀገር በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ መሆን እንዳለበትም አስረድተዋል።

LEAVE A REPLY