ግብፅ የምታሰማውን የተዛባ ለማስተካከል እየተሠራ መሆኑን ደመቀ መኮንን ገለጹ

ግብፅ የምታሰማውን የተዛባ ለማስተካከል እየተሠራ መሆኑን ደመቀ መኮንን ገለጹ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ግብፅ በህዳሴው ግድብ ላይ እያሰማች ያለውን የተዛባ አመለካከት ለማስተካከል ጠንካራ የዲፕሎማሲ ሥራ እንደሚሠራ ተገለጸ።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የሥራ አስፈጻሚ አባላት ትናንት ባካሄዱት መደበኛ ስብሰባ ግድቡ ከኃይል ምንጭነት በተጨማሪ የወንዙን ጂኦ ፖለቲካ እንደሆነም ተሰምቷል።
የሥራ አስፈጻሚ አባላቱ ግብጽ በግድቡ ዙሪያ እያከናወነች ያለውን የተዛባ ትርክት ማስተካከል እንደሚገባ አንስተው የተወያዮ ሲሆን፤ ግብጽ ግድቡን ዓለም ዐቀፍ የጸጥታ ስጋት አድርጋ በማቅረብ በተለይ የአረብ ሀገራትን ድጋፍ ለማሰባሰብ እየሠራች መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገልጸዋል።
ስለ ግድቡ የሚደረጉ የተግባቦት ሥራዎችን በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ በመምራት የኢትዮጵያን ትክክለኛ አቋም ለዓለም ማሳወቅ እንደሚገባም አባላቱ የተናገሩ ሲሆን፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በበኩላቸው በዓለም ላይ ያሉ ድንበር ተሻጋሪ ተፋሰሶች ተሞክሮ የሚያሳየው የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ወንዙን በመጠቀም ደረጃ የተሻለ እድል ይኖራቸዋል ብለዋል።
ኢትዮጵያ የያዘችውን ሀቅ ለዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ የማስረዳቱ ሥራ በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚሠራ የተናገሩት ደግሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፤ ከዚህ በተጓዳኝ በግድቡ ዙሪያ ጠንካራ ሀገራዊ አንድነት ለመፍጠር መሥራት እንዳለበትም ነው ያሳሰቡት።
ግድቡ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንዳለው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ አንጻር የግድቡን ደህንነት የሚያስጠብቁ የአረንጓዴ አሻራ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ከማቅረባቸው ባሻገር፤ ግድቡ ይዟቸው የመጡ የኢኮኖሚ እድሎችን ለመጠቀም ከወዲሁ በተደራጀ መልኩ እንዲሠራም አሳስበዋል።

LEAVE A REPLY