ኦቦ ዳውድ ኢብሳ ሊታሰሩ ነው፤ ቦሌ የሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በፌደራል ፖሊስ አባላት...

ኦቦ ዳውድ ኢብሳ ሊታሰሩ ነው፤ ቦሌ የሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በፌደራል ፖሊስ አባላት ተከቧል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከ40 ዓመታት በላይ ያለ ምንም ውጤት በጫካ ትግል ውስጥ የሰነበተውና በለውጡ ማግስት በሰላማዊ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ የገባው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ-መንበር የሆኑት የአቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት በፖሊስ ተከበበ።
 የፓርቲው ቢሮ ኃላፊ አቶ ገዳ ኦልጅራ ቦሌ አካባቢ የሚገኘው የዳውድ ኢብሳ ቤት በፌደራል ፖሊሶች መከበቡን ጠቁመው፤ በዛ አካባባ ያለ  የጸጥታ ኃይል (አዲስ አበባ ፖሊስ) የሊቀመንበሩን ደኅንነት ለመጠበቅ እንደተሠማራ ከፖሊስ ተነግሮኛል ሲሉ እርስ በርሱ የሚጋጭ አስተያየት ለቢቢሲ ሰጥተዋል።
ከዛሬ (እሁድ) ከሰዐት በኋላ ጀምሮ የኦነግ ሊቀመንበር ቤት በታጠቁ  የጸጥታ አካላት መከበቡንና ዳውድ ኢብሳም ከመኖሪያ ቤታቸው መውጣትና መግባት ካለመቻላቸው ባሻገር፤ ወደ ውጪ የሚወጡ ከሆነም በጸጥታ ኃይሎቹ በቁጥጥር ሥር ሊውሉ እንደሚችሉ ስጋት እንዳላቸው የኦነግ ጽ/ቤት ሓላፊ አስታውቀዋል።
“ዋና ሊቀመንበራችን በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ነው ያሉት። እንደልባቸው ተንቀሳቅሰው የዕለተ ዕለት ሥራቸውን ማከናወን አልቻሉም”  ያሉት አቶ ገዳ ኦልጅራ፤
 ከአቶ ዳውድ በተጨማሪ በቤታቸው ውስጥ ያሉ የቤተሰባቸው አባላትም ከመኖሪያ ግቢው መውጣትም ሆነ ከውጪ መግባት መከልከላቸውን ገልጸዋል።
 የአቶ ዳውድ ኢብሳ ስልክ ከሦስት ቀናት በፊት ጀምሮ እየሠራ አለመሆኑን የተናገሩት የኦነግ ቃል አቀባይ፤ የፓርቲው ሊቀመንበር (ዳውድ ኢብሳ) ከሦስት ቀን በፊት በፖሊስ ተይዘው እንደነበርም አስታውሰዋል።
የአቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት ለምን እንደተከበበ የሚያውቁት ነገር ስለመኖሩ በቢሲየተጠየቁት ቃል አቀባዮ፤ ፖሊስ ይህን ያደረገው ለእርሳቸው (አቶ ዳውድ ኢብሳ) ደኅንነት ሲባል እንደሆነ ነግሮኛል ካሉ በኋላ፤ “ይሁን እንጂ ሰው እንዳይገባና እንዳይወጣ እየከለከሉ ደኅንነት ለመጠበቅ አይመስልም ። የአቶ ዳውድ ስልክ ስለማይሠራ ከራሳቸው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት አልቻልንም” ብለዋል።
በኦነግ ሊቀመንበር ቤት ዙሪያ እየሆነ ያለውን ነገር ለማጣራት ቢቢሲ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ጄይላን አብዲ ጠይቆ የነበረ ቢሆንም፤ እርሳቸውም ስለጉዳዩ ምንም ዓይነት መረጃ እንደሌላቸው ከመናገር ውጪ በቂ ማብራሪያ አልሰጡም።
በቅርቡ የሀጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ በኦሮሚያ ክልልና በአዲስ አበባ የደረሰውን ጥቃትና ውድመት ተከትሎ የተለያዮ የኦነግ አመራሮች የተያዙ መሆናቸውን የሚያስታውሱ የፖለቲካ ተንታኞች ሁለት ቦታ ረግጦ (በጫካ ትግልና ሰላማዊ መንገድ) ሀገር እያመሰ ነው የሚባለው የኦነግ ሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ መታሰራቸው እንደማይቀር በመናገር ላይ ናቸው።

LEAVE A REPLY