የህወሓት ተፅዕኖ ከብዶኛል ያለው የትግራይ ቲቪ ጋዜጠኛ ከመቀለ ሸሽቶ አዲስ አበባ ገባ

የህወሓት ተፅዕኖ ከብዶኛል ያለው የትግራይ ቲቪ ጋዜጠኛ ከመቀለ ሸሽቶ አዲስ አበባ ገባ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አምባገነኑ ህወሓት በትግራይ ክልል የሚያደርሰውን ተፅዕኖ በመጥላት የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች በየጊዜው እያፈነገጡ መሆናቸው እየተነገረ ነው።

በክልሉ የጡረተኛና የሴረኛ ታጋዮቹን ጨፍልቀህ ግዛ ሥርዓት ገርስሶ ለመጣል የሚደረገው የትግራይ ወጣቶች እንቅስቃሴ ውስጥ ውስጡን በፈንቅል አደረጃጀት ተጠናክሮ የቀጠለ እንደሆነም ከአካባቢው የሚወጡ የተለያዮ ፍንጮች ይጠቁማሉ።
ሰሞኑን የትግራይ ክልል ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ የሆነው ቴዎድሮስ አለማየሁ በትግራይ ቴሌቭዥን ውስጥ ባለው ጫና የተነሳ ሥራውን መልቀቁ ታውቋል።
የአንድ ሰው ስምን ማጥፋት እና የአማራን ሕዝብ ከማብጠልጠል የዘለለ የሚዲያ ስነ ምግባርን ያሟላ ዘገባዎች ማቅረብ የተሳነው የትግራይ ቲቪ ዜና አንባቢ የሆነው ቴዎድሮስ አለማየሁ ሥራውን ይሠራበት ከነበረው መቐለ ከተማ በመጥፋት አዲስ አበባ እንደገባም ተረጋግጧል።
“በትግራይ ክልል ቴሌቭዥን ጣቢያ ለሁለት ዓመታት የነበረኝ ቆይታ የሙያ ነፃነትና ሥነ ምግባርን የጣሰ ነው። በሥራችን ላይ ህወሓት  ከፍተኛ የሆነ ተፅዕኖ  አለብን። ሥንሠራ የነበረው መረጃዎችን ለሕብረተሰቡ ማቀበል ሳይሆን የሐሰት ፕሮፐጋንዳ ነው” በማለት የድርጅቱን መሰሪነት ያጋለጠው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አለማየሁ ፤ የትግራይ ቲቪን የተቀላቀለው ከሁለት ዓመት በፊት በቀረበለት የትግራይ ክልል መንግሥት ጥሪ እንደነበርም ተናግሯል።

LEAVE A REPLY