ሀብታቸውን ያላስመዘገቡ ባለሥልጣናት ስማቸው እየተጠቀሰ ለሕዝብ ይፋ ሊደረጉ ነው

ሀብታቸውን ያላስመዘገቡ ባለሥልጣናት ስማቸው እየተጠቀሰ ለሕዝብ ይፋ ሊደረጉ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሀብት መጠናቸውን ያላስመዘገቡ  የመንግሥት ባለሥልጣናት ስም ዝርዝር በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ተባለ።

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን እንደ ገለጸው ከሆነ 90 በመቶ የሚሆኑ የመንግሥት ተሿሚዎች ፣ የሕዝብ ተመራጮችን ጨምሮ  የሀብት ምዝገባዉ የሚመለከታቸዉ አካላት፤ ሀብትና የገቢ ምንጫቸውን አስመዝግበዋል።
በኮሚሽኑ የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መስፍን በላይነህ ፣ በበጀት ዓመቱ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ የ84 ሺኅ 460 ሀብት አስመዝጋቢዎችን ሀብትና የገቢ ምንጭ ለመመዝገብ መታቀቡን ጠቁመው፤
ኮሚሽኑ የሀብት ምዝገባዉ መጠናቀቂያ ቀን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ መሆኑን ገልጾ የነበረ ቢሆንም ፤ በሀገሪቱ ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት ሀብታቸውን ማስመዝገብ ያልቻሉ አካላት አስከ ሀምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም እንደተራዘመ አስታውቋል።
አሁንም በእነዚህ ቀሪ ቀናቶች ምዝገባውን ያልከወኑ 10 በመቶ የመንግሥት ተሿሚዎች ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ጥሪ መቅረቡን የገለጹት እንደ አቶ ተስፋዬ የሀብት መጠናቸውን ያላስመዘገቡ ተሿሚዎች በስምም ሆነ በተቋማቸው ስለተለዮ ደብዳቤ እንዲደርሳቸው ተደርጓል ብለዋል፡፡
ይህንኑ በመገንዘብ በቀሩት አጭር ቀናት ውስጥ ሀብታቸውን የማያስመዘግቡ ከሆነ ኮሚሽኑ ስም እየጠቀሰ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ለመጨረሻ ጊዜ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

LEAVE A REPLY