በአማራ ክልል 405 ሰዎች በሠላም፣ 686ቱ በኃይል እጅ እንዲሰጡ መደረጉ ተገለጸ

በአማራ ክልል 405 ሰዎች በሠላም፣ 686ቱ በኃይል እጅ እንዲሰጡ መደረጉ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አማራ ክልል የሰኔ 15 2011 ዓ.ም ጥቃት ከፈጠራቸውና ከነበሩበት የሠላም ችግሮች በአንጻራዊነት ተላቋል ተባለ።

አፍራሽና ለውጥ አደናቃፊ የሆኑ ኃይሎች፤ በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች የጥፋት አጀንዳ እና የማንነት ጥያቄዎችን በማንሳት አለመረጋጋት ለመፍጠር ሞክረው ነበር ያሉት አቶ ተመስገን ጥሩነህ፤  በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና በአንዳንድ ሥፍራዎች ችግር በመፍጠር ግጭት እንዲከሰትና በሰው ሕይወት፣ እንዲሁም በንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ መደረጉን ገልጸዋል።
 “በማኅበራዊ የትስስር መድረኮች ላይ የሚለቀቁ ሐሰተኛ ትርክቶችን በማሰራጨት ክልሉን ወደ ትርምስ ለማስገባት ሁሉን ዐቀፍ መንገዶችን ሲጠቀሙ ቆይተዋል” ያሉት ርዕሰ መስተዳደር፤ የክልሉን ሰላም ለማደፍረስ ከሚንቀሳቀሱት መካከል በተለይ “የቅማንት ኮሚቴ ነኝ ” በሚል ጥላቻን ካነገቡ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት ፣ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ፣ ትራንስፖርት እንዲቋረጥና በከተሞች ነውጥ እንዲሰፍን ያደረጉት ጥረት በቁጥጥር ሥር ሊውል መቻሉን አስረድተዋል።
በአማራ ክልል አንዳንድ ሥፍራዎች ላይ ሰላም ለማስፈን  እርቀ ሰላም እንዲፈጠር መደረጉን ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳደር፤ ችግር ሲፈጥሩ የነበሩ ያሏቸው 387 ሰዎች በምህረት እንዲገቡ ተደርጎ አንጻራዊ ሠላምና መረጋጋት ለመፍጠር መቻሉን ከመግለጻቸው ባሻገር፤ “የፋኖን ስም በመጠቀም በሁሉም አካባቢዎች  ሕዝብ ላይ ችግር በመፍጠር፣ መንግሥት ሕግን ማስከበር የማይችል ለማስመሰል ተሞክሯልም” ብለዋል።
ሕግና ሥርዓት ለማስከበር በተደረገው ጥረት 215 በምህረት ሲገቡ 405 ሠላማዊ በሆነ መንገድ እጅ የሰጡ ሲሆን፤ ፈቀደኛ ያልነበሩ 686 ሰዎች ደግሞ በኃይል እጅ እንዲሰጡ መደረጉ ታውቋል።

LEAVE A REPLY