ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በኤሌክትሪክ የሚሠራ መኪና ከማራቶን ሞተርስ ተበረከተላቸው

ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በኤሌክትሪክ የሚሠራ መኪና ከማራቶን ሞተርስ ተበረከተላቸው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኤሌክትሪክ ኃይል አማካኝነት የምትሠራ  ዘመናዊ መኪና በስጦታ ተበረከተላቸው።

መኪናዋ የሀዩንዳይ ኩባንያ አካል በሆነው ማራቶን ሞተርስ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ የተገጣጠመች የመጀመሪያ መኪና መሆኗም ተሰምቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለሀዩንዳይ ፕሬዚደንት ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት፣ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን የመገጣጠም ሥራ መጀመሩን ተከትሎ የተለያዮ  በኤሌክትሪክ የሚረሠሩ መኪኖች በቅርቡ በብዛት ይመረታሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በስጦታ የተበረከተላቸውን  ሙሉ በሙሉ በባትሪ የሚሠራውን እና የካርቦን ልቀት የማያስከትለውን መኪና በተቀበሉበት ሲቀበሉ፤ ይህን የመሳሰሉ የመዋለ ነዋይ ፍሰት የሚያስገኙ ሥራዎች በሀገራችን የአየር ንብረት ለውጥን ከመቋቋም ባሻገር፣  ለአረንጓዴ ልምላሜ ከፍተኛ ድጋፍ አሶተዋፅዖ እንደሚኖረው አስረድተዋል።
በኢትዮጵያ የተገጣጠመው መኪናን ለየት የሚያደርገው፣ የተለየ የኃይል ማደያ ሳያስፈልግ በየትኛውም ቦታ ባትሪውን ለመሙላት መቻሉ ነው ተብሎለታል።
“የኢትዮጵያን ልምላሜ ለመጨመር፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለማሻሻል (በአረንጓዴዐሻራ እንቅስቃሴ)፣ እንዲሁም በሸገር እና በእንጦጦ ፓርኮች ተጨባጭ ተግባራትን እየከወንን እንገኛለን። ዛሬ ጠዋት ከእነዚህ ሥራዎች ጋር የተስማማ፣ በማራቶን ሞተርስ አማካኝነት ሙሉ ለሙሉ በሀገራችን የተገጣጠመ፣ የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ መኪና በስጦታነት በመቀበሌ አመሰግናለሁ” ሲሉ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ የካርቦን ልቀት የማያስከትሉ መኪኖች፣ በማደግ ላይ ባሉ ከተሞቻችን የአየር ብክለት እንዲቀንስ ሚናቸው የጎላ ነው ብለዋል።

LEAVE A REPLY