ጨፌ ኦሮሚያ 90 ቢሊዮን ብር በጀት እና አዳዲስ ሹመቶችን አፀደቀ

ጨፌ ኦሮሚያ 90 ቢሊዮን ብር በጀት እና አዳዲስ ሹመቶችን አፀደቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ትናንት የተጀመረው ጨፌ ኦሮሚያ ለቀጣዮ  ለ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት 90 ቢሊየን ብር በሙሉ ድምፅ ማፅደቁ ተነገረ።

ከፀደቀው በጀት ውስጥ 39.57 ብር ተዘዋዋሪ በጀት ሲሆን፣ 50.43 ብር ደግሞ ለወረዳ እና ከተማ አስተዳደር በጀት ሆኖ እንደተመደበ ታውቋል።
ጨፌ ኦሮሚያ በ5ኛ ዓመት 5ኛ የሥራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባዔ አባላት በንፁህ መጠጥ ውሀ እና ፍሳሽን አስመልክቶ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ለውሳኔ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ሙሉ በሙሉ አፅድቀዋል።
በጉባዔው የተለያዩ የሥራ ሓላፊዎች ሹመት ያፀደቀ ሲሆን በዚህ መሠረት፤ ዶ/ር መንግሥቱ በቀለ ሁሪሳ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ሓላፊ፣ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ጎዳና የኦሮሚያ መሬት አጠቃቀም እና አስተዳደር ቢሮ ሓላፊ፣ ወ/ሮ መስከረም ደበበ የኦሮሚያ ገቢዎች ባለሥልጣን ዋና ዳሬክተር፣  አቶ አህመድ ሰዒድ ኡመር የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ማኅበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ሓላፊ ሆነው መሾማቸው ተሰምቷል።

LEAVE A REPLY