ብሔራዊ የሎጀስቲክ ምክር ቤት ዛሬ በይፋ ተመሠረተ

ብሔራዊ የሎጀስቲክ ምክር ቤት ዛሬ በይፋ ተመሠረተ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ችግሮች ዘላቂነት እና ሥርአት ባለው መንገድ ለመፍታት፣ በዘርፉ ቁልፍ ሚና ያላቸውን የመንግሥት ተቋማት እና የግሉን ዘርፍ ያካተተ ብሔራዊ የሎጂስቲክስ ምክር ቤት እንደተቋቋመ ነው የተነገረው።

ምክር ቤቱን ምስረታ በይፋ ለማብሰርና በቀጣይ አሠራሮቹ ላይ ግልጽነት ለመፍጠር ከባለድርሻ አካላት ጋር የምስረታ ጉባኤ ተካሂዷል።
በምስረታ ጉባዔው ላይ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ፤ ሌሎችም የመንግሥት እና የግሉን ዘርፍ ተወካዮች የተገኙ ሲሆን፤ ሚኒስትሯ በወቅቱ ውስብስብና የማይደፈር የሚመስለው የሎጂስቲክስ ዘርፍ ግልጽ፣ ፈጣንና ዘመናዊ ሥርዓትን ሊተገብር እንደሚገባው ተናግረዋል።
የብሔራዊ ሎጂስቲክስ ምክር ቤት በዘርፉ የተቀናጀ አሠራር መኖሩን የሚያረጋግጥ ከመሆኑ ባሻገር፤
 በሎጂስቲክስ ዘርፍ እንቅፋት የሆኑ አሠራሮችን በመለየት የእርምት እርምጃዎች እንዲወሰዱ ያደርጋል ነው የተባለው።

LEAVE A REPLY